፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 24 2016| NBC ETHIOPIA-በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች የተገነቡ ሎጅና ሪዞርቶች ለክልሎች ተላልፈው በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ስር እንዲተዳደሩ የሚያደርግ ሰምምነት ተፈረመ፡፡
-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ከ255 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸውና ለአቅመ ደካማ የከተማዋ ነዋሪዎች ማዕድ አጋርተዋል።
-የሀገር ውስጥና የውጭ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።
-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በትንሳኤ በዓል ዋዜማና ዕለት የኃይል መዋዥቅና መቆራረጥ ለመቀነስ፤ ከተከሰተም አፋጣኝ ምላሽ ለመሰጠት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።
-በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር ኢ/ር) በአጎዋ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ የአሜሪካ የኮንግረስ አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












