ከሰሞንኛ አስገራሚ እና አነጋጋሪ ጉዳዮች ጥቂቶቹን እንካችሁ ልንላችሁ ወደድን፡፡እድለኛው የካንሰር ታካሚ በሚል ርእስ ሆኗል፣ በሀገረ አሜሪካ የ1.3 ቢሊዮን ዶላር የሎተሪ እድል አሸናፊው የካንሰር ታማሚ ነው፡፡ስምንት አመታት በካንስር ሲሰቃይ የነበረው ቸንግ ቻርሊ ሳይፋን የተባለው ግለሰብ በዚህ ወር የወጣውን የ1.3 ቢሊዮን ዶላር ጃክፖት ሎተሪ ካሸነፉት ሶስት እድለኞች አንዱ ሆኗል።
የኦሪጎን ሎተሪ አስተዳደር እንዳለው ይህ የ1.3 ቢሊዮን ዶላር ሽልማት በታሪክ አራተኛው ግዙፍ የፖወርቦል ጃክፖት ሲሆን በአሜሪካ የሎተሪ ታሪከ ውስጥ ደግሞ ስምንተኛና ትልቁ አሸናፊ ነው፡፡
ሎተሪዉን ቸንግ ቻርሊ፣ ባለቤቱና ጓደኛው አዋተው መገዛታቸውን ገልጸዋል፡፡ ግማሹን ገንዘብ እሱ እንደሚወስድ እና ግማሹን ለጓደኛው እንደሚሰጣት ተናግሯል፡፡ባል እና ሚስቶቹ ከታክስ በኋላ 422 ሚሊዮን ዶላር በእጃቸው ያስገባሉ ነው የተባለው።

ቤተሰቤን መርዳት እና መታከም እችላለሁ ያለው ሳይፋን ህመሙን ለመታከም ጥሩ ዶክተር እንደሚያገኝ ጨምሮ ገልጿል። የሁለት ወጣት ልጆች አባት የሆነው ሳይፋን የካንሰር ህመምተኛ በመሆኑ ይህን ሁሉ ገንዘብ ምን አደርገዋለሁ ምን ያህል ይሆን የምኖረው ሲል መጨነቁም ተሰምቷል፡፡
ሎተሪ ሊወጣ ሳምንት ሲቀረው የሎተሪ ቁጥሩን በብጫቂ ወረቀት ላይ ከጻፈ በኋላ በትራሱ ስር አድርጎ ለማሸነፍ ጸሎት ሲደርግ እንደነበር ገልጿል።
በግዙፍ ቢልቦርድ የትዳር አፋልጉኝ ማስታወቂያ ያስነገረው አሜሪካዊ የሰሞኑ የአለም መነጋገሪያ ስለመሆኑ NewYork post አስነብቧል፡፡
400 ዶላር የሚከፈልበት ግዙፍ የሚስት አፋልጉኝ ማስታወቂያ የለጠፉት ግለሰብም አሜሪካዊ ናቸው ተብሏል፡፡

ሰዎች ከትዳር አጋራቸው ጋር በአንድም በሌላም መንገድ መገናኘታቸው የተለመደ ነው፡፡ በተለይ ወቅቱ በዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂ ተገናኝተው የሚጋቡ ጥንዶች የበረከቱበት ነው፡፡
ነገር ግን ከወደ አሜሪካ የተሰማው የትዳር አፋልጉኝ ወሬ ሰዎችን ያስገረመ ሆኗል፡፡ በቴክሳስ ነዋሪ የሆኑት የ 70 አመት አዛውንት በሳምንት 400 ዶላር የሚከፈልበት ግዙፍ የሚስት አፋልጉኝ ማስታወቂያ መለጠፋቸው እጅን በአፍ የሚያስጭን ሆኗል፡፡
ብቸኝነት ያሰለቻቸው ኤአይ ጊልበርቲ የተሰኙት አዛውንቱ የትዳር አጋር የማግኘት ምኞታቸውን እውን ለማድረግ በሳምንት 400 ዶላር የሚከፈልበት ግዙፍ ቢልቦርድ ላይ ምስላቸውን፣ ስልካቸውን እንዲሁም የኢሜል አድራሻቸውን ያሰፈሩበትን ማስታወቂያ እንዲለጠፍ አድርገዋል።
ማስታወቂያው ከተለጠፈ በኋላ በሁለት ሳምንት ብቻ ከ400 በላይ የስልክ ጥሪዎች እንዲሁም ከ50 በላይ የኢሜል መልዕክቶች እንደደረሳቸው ይናገራሉ። ይሁን እንጂ አንዳቸውም መስፈርታቸውን የሚያሟሉ ሆነው እንዳላገኟቸው ነው የገለጹት።
ታማኝነት፣ ሃቀኝነት እና ትህትና የማልደራደርባቸው ቀይ መስመሮች ናቸው የሚሉት አዛውንቱ አብዛኞቹ የስልክ ጥሪዎች ያላቸውን ሃብት ታሳቢ ያደረጉና ወጪዎችን ሸፍኑልኝ የሚሉ ናቸው ማለታቸውን ኒዮርክ ፖሰት በገጹ አስነብቧል።
ብቸኛ ነኝ የትዳር አጋር እፈልጋለሁ የምፈልጋትን አይነት ሴት ካገኘሁ የመኖሪያ አድራሻዬን ለመቀየር ዝግጁ ነኝ ማለታቸውም ተገልጿል ።ከቀድሞ የትዳር አጋራቸው አንድ ልጅ ያገኙት አዛውንቱ የቀድሞ የትዳር አጋራቸውን በ26 አመት እንደሚበልጧቸው በማውሳትም ለእድሜ ልዩነት ቦታ እንደማይሰጡ እና እንደ እድሜያቸው ሳይሆን በጥሩ አቋም ላይ መገኘታቸውን ለራሳቸው ምስክርነት የሰጡት፡፡
ሌላኛው አስገራሚ ዜናችን ወደ ሀገረ ቻይና ያመራናል ፡፡ በቻይና የምትኖር አንዲት ሴት ለ27 አመት ወጣት ልጇ ሚስት ለማደረግ የአስራ አንድ አመት ታዳጊ ህጻን አፍና መውሰዷ ነው የተነገረው፡፡
ያንግ የተባለችው ግለሰብ ወደ ገጠሩ ክፍል በማቅናት ለልጇ ጥሩ ሚስትን ለማሳደግ በማሰብ የአስራ አንድ አመቷን ህጻን ቤተሰቦች ልጃቸውን እንዲሰጧት ትጠይቃለች ነገር ግን የህጻኗ አባት አይሆንም ብሎ ይመልሳታል፡፡

በልጅቱዋ አባት መልስ ያልተደሰተችው ያንግ ከ 27 አመት ልጇ ጋር በመሆን ህጻኗን ከቤቱዋ እንደጠለፏት ኦዲቲ ሴንተራል አስነብቦል፡፡ ህጻኗን አግተው ወደ ቤታቸው ከወሰዱ ከስድስት ቅን በኃላ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል፡፡
ያው እንግዲህ እንደ እናት በመልካም ስብዕና የታነጸች ልጅ በማሳደግ ለልጇ ለመዳር ካላት በጎ ፍላጎት ነው ብሎ ያለፋት ህግ የለም፡፡
በሰሩት ወንጀል ፍርድ ቤት ተገትረው እናት በሁለት አመት እሰራት ስትቀጣ፣ ተባባሪ የነበረው ልጇ ደግሞ በሰባት ወር እስራት እንዲቀጡ ተፈርዶባቸዋል፡፡ ጉዳዩ በማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ከወጣ በኃላ በርካቶች ቅጣቱ ለሰሩት ወንጀል ተገቢ እንዳልሆነ እየገለጹ ይገኛሉ፡፡












