፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 23 2016| NBC ETHIOPIA-የበርካታ ህዝቦች መኖሪያ በሆነችው ሀገረ ህንድ ያልተለመዱ እምነቶች ፤በአላትን እንዲሁም ልዩ ልዩ ባህላዊ ክንዋኔዎች ይዘወተሩባታል፡፡
በደቡባዊ የህንድ ግዛት ካራናካታ የሚገኙ ህዝቦች የሚከወነው የሜድ ሳናና ሀይማኖታዊ ክንውን ግን ከባህልነት ባለፈ የበርካቶችን ትኩረት የሚስብ እና ቁጣን የሚቀሰቅስ ሆኖ እስከዛሬ ዘልቋል፡፡
በዚህ ሀይማኖታዊ ክንውን አማኞች ሰብራህማኒያ ወደተሰኘው መቅደስ በማቅናት ሀይኖማታዊ ስርአትን ከከወኑ እና ለቡድሀ ምስጋናን ካቀረቡ በኋላ ወደ አንዱ ወንዝ ዳር በማቅናት ተሰባስበው በጋራ ይመገባሉ፤ በመቀጠልም ለምግብነት ከሚውል ጥሩ ምግብ በብዛት ከተዘጋጀ በኋላ ላይ ልብሳቸውን በማውለቅ ይንከባለላሉ፡፡
ይህ ከ 500 አመታት በላይ እንደዘለቀ የሚነገርለት ሀይማኖታዊ ሁነቱ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ስፍራን የሚሰጠው ክንውን ነው፡፡

የእምነቱ ተከታዮች የሚያከናውኑት ተግባር ከሀይማኖታዊ ትሩፋቱ ባሻገር ከቆዳ በሽታ ፤ ከመካንነት እንዲሁም በዘር ከተላለፈ እርግማ ይጠብቀናል ብለው ያምናሉ፡፡
በዚህ ሀይኖማታዊ እና ባህላዊ ሁነት በሁለት ጎራ በተከፈሉ ሰዎች ድጋፍ እና ትችትን ሲያቀርቡበት ይስተዋላል ፤ለባህሉ ባለቤቶች የመብት ጥያቄ ለአንዳንዶች መዝናኛ፤ የቱሪስት መሳቢያ ሲሆን ሌሎች ከኢሞራላዊ ድርጊት ነው ሲሉም ይተቹታል፡፡
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2010 የሀገሪቱ ማህበራዊ አንቂዎች እና አክቲቪስቶች የክልሉ መንግስት ድርጊቱን እንዲከላክል እና አዋጅ እንዲወጣበት በርካታ ንቅናቄዎችን ሲያደርጉም ቆይተዋል፡፡

ይህ በምግብ ላይ የመንከባለል ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ድርጊት ለአካባቢ ብክለት ከመዳረግ ባሻገር ከሰዋዊነት የወጣ ተግባር ነው በማለት የማህበራዊ ባለሞያዎች ትችታቸውን በየግዜው ቢያቀርቡም የእምነቱ ተከታዮች ማንንም አንሰማም ቢል ስሜት መንግስት እና የመንግስት አካላት ከሀይማኖታዊ ስርአት መራቅ አለባቸው በማለት ዛሬም ሀይማኖታዊ ስርአቱን መከናወናቸውን ቀጥለዋል፡፡
አስቡት ይህ ሃይማኖታዊ ስነስርዓት የሚከወንባት ሀገረ ህንድ እንደ የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት የዓለም የምግብ ዋስትና እና የተመጣጠነ ምግብ ሁኔታ የ2022 ሪፖርት 224.3 ሚሊዮን ሰዎች ወይም 16 በመቶው ሕዝቧ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያለባቸው ናቸው፡፡
መሽቶ እስኪነጋም በርካታ አስገራሚ ሁነቶች ሳይከናወን እና ሳይሰማ በማይታደርባ ሀረገ ህንድ ወቸው ጉድ ያሰኘንን ምግብ ላይ የመንከባለል ሀይማኖታዊ ክንውን አስቃኘናችሁ፡፡
በ-የአብስራ ሚሊዩን
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Website – https://nbcethiopia.com/news/
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












