Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

በአራት እግር የሚጓዙት የኡላስ ቤተሰቦች

April 27, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ሚያዚያ 19 2016| NBC ETHIOPIA- አሁን ባለንበት በ 21ኛው ክፍለ ዘመን የሰው ልጆች አመጣጥ ተብለው ከሚታመኑት አንዱ የሆነው የዝግመተ ለውጥ ሂደት ወይንም The evolution theory እውን መሆኑን ማሳያ እንዲሁም በሰው ልጆች እና በጎሬላ መካከል የነበረውን የዝግመተ ለውጥ ሂደት እንደ ማረጋገጫ ተደርገው የሚቆጠሩ የቤተሰብ አባላት አሉ ቢባል ለሰሚውም ግራ የሚያጋባ ነው፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው በደቡብ ምስራቅ ቱርክ ራቅ ባለ የገጠራማ ስፍራ ለበርካታ አመታት እራሳቸውን ከማህበረሰቡ አግለው የሚኖሩ 19 የቤተሰብ አባላት አሉ፡፡

የኡላስ ቤተሰብ ተብለው የሚጠሩት የቤተሰብ አባላት 12ቱ እንደማንኛውም ሰው ጤነኛ የእድገት ስርአትን የተከተሉ ሲሆኑ፣ አምስት ሴቶች እና በህልፈት የተለያቸውን ጨምሮ 2 ወንድ የቤተሰቡ አባላት እድሜያቸውን ሙሉ በመዳፎቻቸው እና በእግሮቻቸው እንደ እንስሳት እየዳሁ መሄድን ተገደዋል፡፡

ወላጅ እናታቸው በልጅነታቸው እንደማንኛውም ህጻን ይድሁ እንደነበር እና ከፍ ሲሉ ቆሞ ከመራመድ ይልቅ በመዳፎቻቸው እና በእግራቸው መራመድ መጀመራቸውን ትናገራለች፡፡

‹‹እስከ 9 ወራቸው ድረስ እንደማንኛውም ህጻን እንዲህ ነበር የሚድሁት፤ ከፍ እያሉ ሲመጡ ግን ቀና ማለት ከነሱ እራቀ ሙሉ ለሙሉ በእጅ እና በመዳፋቸው  መሄድ ጀመሩ››፡፡

ከ 18 እስከ 34 አመት እድሜ የሚገኙት የኡላስ ቤተሰብ አባላት የልጅነት ጊዜያቸውን በደስታ ማሳለፍ አልታደሉም፡፡ ላለፉት በርካታ አመታት ከማህበረሰቡ ተገለው እና ተደብቀው ነው የኖሩት፤ ቤተሰቦቻቸው እነርሱን ለማሳደግ ብዙ ፈተናዎችን እንዳሳለፉም ይናገራሉ፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ስለኡላስ የቤተሰብ አባላት የተሰማው፣ የቱርክ ሳይንሳዊ የጥናት መፅሄቶች ባስነበቡት ጽሁፍ ነበር፤ ይህንን ተከትሎ ቢቢሲ ቴሌቪዥን ወደ ወደቤተሰቦቹ መኖሪያ መንደር በማቅናት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2005 The family that walk on all four የተሰኘ ዶክመንተሪ አሰናድቶ ቤተሰቡን ለዓለም አስተዋውቋል፡፡

የኢቮሊውሽነሪ ሳይኮሎጂስት ባለሞያው ፕሮፌሰር ኒክ ሀምፍሬይ እንደዚ አይነት ሁነት በህይወታቸው አጋጥሟቸው እንደማያውቅ እና በቱርክ የጤና መፅሄቶች ላይ ታሪኩን ለመጀመሪያ ጊዜ ካነበቡበት ወዲህ ስለቤተሰቡ ለማወቅ ጉጉት እንዳደረባቸው ይናገራሉ፡፡

የኡላስ ቤተሰብ ለዓመታት እራሳቸውን አግልለው በገጠራማ መንደር መኖራቸው እና ወላጆቻቸው ቢሆኑ እድሜያቸው የገፉ መሆኑ ፣ ጠንከር ያለ ህክምና እንዳያገኙ እንዲሁም ከሌሎች ሰዎችም መራመድ የሚያግዛቸው መደገፊያዎችን እንዳያገኙ አድርጓቸዋል፡፡

ሳይንቲስቶች የኡላስ ቤተሰብ አባላት ጉዳይ ከሰሙበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ምርምሮችን አድርገዋል፡፡ ይሁንና የቤተሰቡን አካላዊ አፈጣጠር ወሰብሰብ ያለ በመሆኑ ይህ ነው የሚል መላምት ላይ ለመድረስ መስጠት አዳጋች እንደሆነባቸው ይናገራሉ፡፡ አጥንቶቻቸው ከሰው ልጆች የአጥንት አወቃቀር የተለየ እና ያልተለመደ እንደሆነ በእንግሊዝ ሊቨርፑል ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆኑ ሳይንቲስቶች ይናገራሉ፡፡ ሆኖም ሴረብለም በተባለው የአዕምሮ ክፍላቸው  ላይ ከተፈጠረ ችግር ጋር ተያይዞ የተከሰተ ሊሆን ይችላል በሚል ግምት ምርመራ ቢደረግም አዲስ ውጤት ማግኘት አልተቻለም፡፡

በምርመራ ሂደቱ እና እየተደረገላቸው ባለው ክትትል አብዝኞቹ ደስተኛነታቸውን ቢገልጹም፣ ሁሴን የተባለው የቤተሰቡ አባል ግን  ጊዜው እንደረፈደ እና ምንም አይነት ለውጥ እንደማይመጣ በቁጣው ይገልጻል፡፡

ከኡላስ ቤተሰብ አባላት አፈጣጠር ጀርባ ያለው ሚስጥራዊ እና ግርምትን ጫሪ ሁኔትን በተመለከተ የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች ዛሬም መደምደሚያ ባያገኙም እስካሁን የተሄደባቸው ርቀቶች በትንሹም ቢሆን ለቤተሰቡ እረፍት የሰጠ ይመስላል፡፡

በ-የአብስራሚሊዮን

ShareTweetShare
Previous Post

አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

Next Post

አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
51
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሁለገብ ሕንፃ ግንባታ ተጀመረ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሁለገብ ሕንፃ ግንባታ ተጀመረ

ማያ አንጀሉ

ማያ አንጀሉ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?