፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 18 2016| NBC ETHIOPIA- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል።
በ9 ወራቱ በአደረጃጅት አኳያ የተሻለ አፈጸጸም መኖሩ፤የአሰራር መመሪያዎችን ማስተካከል ላይ ስራዎች መሰራታቸው ተጠቁሟል።

የአሰሪና ሰራተኛን የሚመለከቱ የፖሊስና የህግ ማዕቀፍ ተፈፃሚነት በቁጥጥር ከማረጋገጥ አኳያ 84 በመቶ ተፈጻሚ መሆኑ ተመላክቷል።የአሰሪዎች ማህበራት አደረጃጀት አፈጻጻም ዝቅትኛ መሆኑ እና የሚደራጁ አሰሪዎች ስለስራ አካባቢ ምቹነት ከመምከር ይልቅ የተለይ ጥቅማጥቅምን ለማግኘት ያለመ መሆኑ እንደችግር ተነስቷል።
በበጀት ዓመቱ የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በ – ሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












