፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 18 2016| NBC ETHIOPIA-የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ በ244 ሰራተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱን አስታወቀ።
-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጽዱ ኢትዮጵያን ለመፍጠር አዲስ ተግባርና ንቅናቄ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል።
-ባለፉት ዘጠኝ ወራት በመዲናዋ ለአንድ ሺህ 921 ባለሀብቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷል ተባለ፡፡
-በአዲስ አበባ ከተማ በኮሪደር ልማቱ ተነሺ የሆኑ ዜጎችን ቅሬታ የሚሰማበት አሰራር፣ ቅሬታዎችን ተከታትሎ የሚፈታ እና የቅርብ ክትትል የሚያደርግ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ እየሰራ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡
-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ የብሪክስ ባንክ በሆነው ኒው ደቨሎፕመንት ባንክ አባል ለመሆን እየሰራች መሆኑን አስታወቀ፡፡
-ስዊድን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ላሉ ኢትዮጵያውያን የሚውል ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አስተላለፈች፡፡
-የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚና የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ።
-ዩ ኤን ኤድስ በኢትዮጵያ ያለውን የኤች አይ ቪ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ፡፡
-ቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ያለውን አጋርነት እንደሚያጠናክር ገለጸ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












