የዩቲዩብ የመጀመሪያ ቪድዮ
፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 18 2016| NBC ETHIOPIA- በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የህይወት ጉዞን ማሳየት የቻለ መተግበሪያ ሲሆን ፣ ሰዎች የሚፈልጉትን ነገር በእጃቸው በቀላሉ እንዲያገኙም አስችሏልየዩቲዩብ መተግበሪያ፡፡
ዩቲዩብ እ.ኤ.አ በ2005 ፣ ስቲቭ ቼን፣ ቻድ ሃርሊ እና ጃዌድ ካሪም በተባሉ የቀድሞ የአሜሪካ የኢ-ኮሜርስ ኩባንያ ሰራተኞች ነበር የተዋወቀው፡፡ የመጀመሪያው ተንቀሳቃሽ ምስል የተለቀቀውም ከዛሬ 19 አመታት በፊት ነበር፡፡የመተግበርያው ጅማሮ ሰዎች በእለት ተእለት የሚያልከናውኗቸውን ተግባራት ለሌሎች ለማጋራት እና ልምድ ለመቀስም በማለም ታሳቢ ያደረገ ነበር ፡፡

በዩቲዩብ መተግበሪያ የመጀመሪያውን ውሎ ለተመልካቾች ያደረሰው ግለሰብ ከመስራቾቹ አንዱ ጃዌድ ካሪም ነበር፡፡ ከ 19 አመታት በፊት የተለቀቀው ተንቀሳሽ ምስልም 19 ሰከንድ እርዝማኔ ነበረው፡፡
ተንቀሳቃሽ ምስሉ በመተግበሪያው የተለቀቀውም እ.ኤ.አ ሚያዚያ 23 ልክ ነበር፡፡"Me at the zoo" የሚል ርእስ ያለው የመጀመሪያው ተንቀሳቃሽ ምስል ጃዌድ በካሊፎርኒያ ሳንዲያጎ መካነ አራዊት ውስጥ የነበረውን የቀን ውሎ የሚያሳይ ነው፡፡ ተንቀሳቃሽ ምስሉም ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያገኘው እና ሌሎች ተንቀሳቃሽ ምስሎች እንዲለቀቁ በሩን የከፈተ ነበር፡፡ ሚያዚያ 23 My Snowboarding Skillz የተሰኘው ሁለተኛ ቪዲዮ ሊለቀቅ ችሏል፡፡ ቪዲዮውን 4.1 ሚሊየን ሰዎች ተመልክተውታል፡፡ በማግስቱ ሚያዝያ 24 የተለቀቀው ቪዲዮ Tribute' የተሰኘ ሲሆን 3.1 ሚሊየን እይታን አግኝቷል፡፡
Premature Baldness በሚያዝያ 28 እንዲሁም Carrie Rides a Truck ኤፕሪል 30 በ2005 ዓ.ም በዩቲዩብ የተለቀቁ ሲሆን፣ 611ሺ እና 546ሺ እይታወችን ማግኘት የቻሉሉ ቀደምት ተንቀሳቃሽ ምስሎች ናቸው፡፡

ከ310 ሚሊዮን በላይ እይታዎችን መሰብሰብ የቻለው የመጀመሪያው ቪዲዮ እስከዛሬ ድረስ በካሪም ቻናል የሚገኘው ብቸኛው ቪዲዮ በመሆን ከአስርት አመታት በላይ ማስቆጠር ችሏል፡፡
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ብቸኛው ሰዎች የእለት ተእለት የአኗኗር ዘያቸውን የሚያጋሩበት መተግበሪያ በመሆን በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች መተግበሪያውን መጠቀም ጀምረዋል፡፡
በ3ቱ የቀድሞ የአሜሪካ የኢ-ኮሜርስ ኩባንያ ፔይ ፓል ሰራተኞች የተፈጠረው ዩቲዩብ ከአንድ አመት በኋላ እ.ኤ.አ በ2006 ለ ለጎግል ኩባንያ ተሸጠ ፡፡ ዋና መሥሪያ ቤቱ በሳን ብሩኖ፣ ካሊፎርኒያ ያደረገው የዩቲዩብ ኩባንያ በአሁኑ ሰዓት እጅግ ተወዳጅ ከሆኑ መተግበሪያዎች መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡
እ.ኤ.አ. በ2023 2.49 ቢሊዮን ተጠቃሚዎች እንዳሉት ሪፖርቶች ይጠቁማሉ፡፡ ይህም Google እና Facebook በመከተል በዓለም ላይ ካሉት በጣም ተወዳጅ እና ከፍተኛ ተጠቃሚዎች ካሏቸው መተግበሪያዎች አንዱ እንዲሆን አድርጎታል፡፡












