፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 17 2016| NBC ETHIOPIA- በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ በተከሰተ ጎርፍ መንገዶች በውሃ የተጥለቀለቁ ሲሆን የሀገሪቱ ባለስልጣን የጎርፉ መጠን በከፋ ደረጃ እየጨመረ ነው ብለዋል።
የተባበሩት የመንግስታት ድርጅት ቢያንስ 32 ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ እና ከ40 ሺህ የሚበልጡት ደግሞ በዝናቡ እና ባስከተለው ጎርፍ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለመሸሽ መገደዳቸውን ገልጿል።

በናይሮቢና አካባቢው በርካታ የመኖሪያ መንደሮች በሚጥለው ዝናብ በከፍተኛ ሁኔታ እየተጥለቀለቁ ይገኛሉ።
ኬንያ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትም ባለፉት ሳምንታት በጣለው ከባድ ዝናብ ተጽዕኖ ውስጥ ወድቀዋል ተብሏል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












