፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 17 2016| NBC ETHIOPIA- የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የግሉን ዘርፍ ለመደገፍና የአቅም ግንባት ስራዎችን በቢዝነስ መስኮች ተደራሽ ለማድረግ በቴክኖለጂ የተደገፈ የቢዝነስ ሊደርሺፕ አካዳሚን ይፋ አድርጓል፡፡
የቢዝነስ ሊደርሺፕ አካዳሚን ስልጠናውን ለማካሄድ 230 ሺህ ዩሮ ድጋፍ መደረጉም ተገልጿል፡፡
ስልጠናው የሴቶችን የአመራር ብቃት ለማሳደግ፣ አካል ጉዳተኞችን ተሳታፊ የሚያደርግና ዘመኑን የዋጁ የአይሲቲ ቴክኖሎጂዎችን መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎች ማዘጋጀቱን ገልጿል፡፡
የቢዝነስ ሊደርሺፕ ስልጠናው ማግኘት የሚፈልጉ የንግዱ ማህበረሰብ ባሉበት ሁሉም የአገሪቷ አካባቢዎች ማግኘት እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡
ምክር ቤቱ የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው አበረታች እንቅስቃሴ እንዲኖረው የምርምር፣ የንግድና ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ እንዲሁም የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
ከዚህ ቀደም በነበሩት የቢዝነስ መስክ ስልጠናዎች ከ150 ሺህ በላይ ዜጎች ተሳታፊ መሆናቸው በመድረኩ ተመላክቷል፡፡
በ-ሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












