፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 16 2016| NBC ETHIOPIA- እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ 1970ዎቹ መነሻውን ያደረገው የኒዮርክ ማራቶንን ምሳሌ በማድረግ እንደተጀመረ ይነገርለታል የለንደን ማራቶን
የለንደን ማራቶን መጋቢት 29 ቀን 1981 አመተ ምህረት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ሰዎችን በየዘርፉ የሚያሳትፍ አመታዊ የሩጫ ውድድር በመሆን ዘልቋል፡፡
ውድድሩ በተጀመረበት የመጀመሪያው አመት ላይ ከ22 ሺ በላይ ሰዎች ተሳትፈውበት ነበር፡፡
በወቅቱ ከተጠበቀው የሰዎች ቁጥር በላይ በመሳተፋቸው ብዙዎች ለተለያዩ አደጋዎች እንደተዳጉ እና ጥቂቶች ብቻ ውድድሩን ማጠናቀቅ እንቻሉም በለንደን ኦሎምፒክ ታሪክ ይነገራል፡፡

ከዛን ጊዜ አንስቶ የውድድር አይነቶቹን እና አላማውን በማስፋት የማራቶን ውድድሩ የሚከናወን ሲሆን አዘጋጆቹ አመቱን ሙሉ ሽርጉድ በማለት ያሰናዱታል፡፡
ከመላው አለም የሚገኙ የስፖርቱ ማህበረሰብ እንዲሁም ሌሎች አላማውን ያነገቡ ሰዎች በመሳተፍ ስኬታማ መሆንም ችለዋል፡፡
ለአብነትም በርካታ ጀግና ኢትዮጵያዊ አትሌቶች በተለያዩ ጊዜያት በውድድሩ በመሳተፍ ከራሳቸው አልፈው በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ ስም በመድረኩ ከፍ አርገውበታል፡፡
ከሰሞኑ በተካሔደው የ2024 የለንደን ማራቶን ውድድርም የበርካታ ድሎች ባለቤት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በማራቶን ውድድር የ2ኝነት ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ አይበገሬነቱን ዳግም ያረጋገጠበት መድረክ ሆኖ አልፏል፡፡

ዋናው ቁም ነገሩ ታዲያ የስፖርቱን ማህበረሰብ ከሚያስደተው የሩጫ ውድድር ባሻገር በእለቱ የሚከናወኑ የበርካቶችን ቀልብ የሚይዙ የተለያዩ ሁነቶች ናቸው ፡፡
እነዚህም ዝነኞች፤ ፖለቲከኞች፤ እንዲሁም የተለያዩ በጎ አላማን ያነገቡ ግለሰቦች እና ማህበራት የተለያዩ አልባሳትን በመልበስ የሚሳተፉበት የበጎ አድራጎት መርሀግብር ነው፡፡
በየአመቱ በሚከናወነው ውድድር ላይ አዘጋጆቹ በጎ አድራጎት አላማን አንግበው ለሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች እና ማህበራት የተለያዩ እድሎችን በማመቻቸት ውድድሩ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያደርጋሉ፣ በዚህ ደግሞ የየግል አላማቸውን በመያዝ ታዋቂ እና ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች ይሳተፉበታል አብዛኞች ሊደግፉት የሚፈልጉትን ርዕሰ ጉዳይን በማስተዋወቅ ውድድሩን ይሳተፋሉ፡፡
በዚህም ማህበራቱ ተሳታፊው ቢያውቃቸው የሚሏቸውን ጠቃሚ መልዕክቶች ትኩረት በሚስቡ አልባሳትን ላይ በመጻፍ ውድድሩ ላይ የሚሳተፍ ሲሆን ከዛም ባሻገር እነዛን አልባሳት በመልበስ እስከ ውድድሩ መጨረሻ መስመር ድረስ በመሮጥ ሽልማቶችን በማግኘት የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ገቢ ያደርጋሉ፡፡
በተለያዩ ግዜያት ለካንሰር ህሙማን፤ ለወላጅ አልባ ህጻናት፤ ለአይምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ታዳጊዎች ለመርዳት በረካታ ዝነኛ ሰዎች ተሳትፎን አድርገዋል፡፡
በዘንድሮ አመት ለተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅት ተሳታፊ ከነበሩ ዝነኛ ሰዎች መካከል ኮሜዲያን እና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ ሮሚሽ ራንታን ተሳታፊ ነበር

ሮሚሽ በዚህ ውድድር ላይ ተሳትፎ ያደረገው እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን የመከላከል ዘመቻን ለሚደግፍ ተቋም ነበር፤
ከርሱ ባሻገር ተዋናይት Ruth Wilson እንዲሁም Comedian Joel Dommett በአምባሳደርነት ለሚያገለግሉበት የተለያዩ የበጎ አድራጎት ተቋማት በመሮጥ ገቢ ከሰበሰቡ ዝነኞች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ሌላው በዘንድሮ የ2024 ለንደን ማራቶን 20 የፓርላማ አባላት እና ቻንስለሮች የተሳተፉ ሲሆን ቻንስለር ጀርሚ ሀንት እና የቀድሞ የጤና ሚኒስቴር ጸኀፊ ማት ናንኮክ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ለበጎ አድራት ተቋማት እንደ ወርቃማ እድል የሆነው የለንደን ማራቶን ገቢ ከመሰብሰቢያነት ባሻገር ከተለያዩ የአለም ሀገራት ለሚመጡ ሰዎች ስራዎቻቸውን ለማስተዋወቅ እድልን ይፈጥራል፡፡
ዘንድሮ በተካሄደው የማራቶን ውድድር ለየት ያለው አንዱ ሁነት ለአካል ጉዳተኛ ተሳታፊዎች እና ለሌሎች አካል ጉዳተኛ ያልሆኑ ሰዎች በተወዳደሩበት ውድድር አሸናፊ ለሆኑ ሰዎች የተሰጠው የገንዘብ መጠን ተመሳሳይ መሆኑ ነው፡፡
በነገራችን ላይ ካለፉት ግዜያት ውድድሮች የዘንድሮ አካታች እንደነበር አዘጋጆቹ የገለጹ ሲሆን ከ 200 በላይ የአካል ጉዳተኛ ተሳታፊዎችን እንደተሳተፉበት ገልጸዋል፡
በማራቶኑ ለመሳተፍ ወደ ሀገረ እንግሊዝ የተጓዙት ተሳታፊዎችን ምቾት የጠጠበቀ ይሆን ዘንድ ለንደን የሃይማኖት ስርአት ማከናወኛ ቦታዎችን እና እናች ልጆቻቸውን የሚያጠቡበት ስፍራዎችን አዘጋጅታለች
ያለፈው የፈረንጆቹ 2023 በተካሄደው የማራቶን ውድድር በዓለማችን በአንድ ቀን ከተሰበበሰቡ የገቢ ማሰባሰቢያዎች ከፍተኛውን መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን በዚህም የተገኘውን 63 ሚሊዮን ፓውንድ በሺዎች ለሚቆጠሩ የበጎ አድራጎት ተቋማት ማከፋፈል ተችሏል፡፡
በ-የአብስራ ሚሊዮን












