፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 25፣ 2016| NBC ETHIOPIA-የቅርስ ጥናት እና ባለስልጣን በፒያሳ እና አከባቢ በመንገድ ዳር ኮሊደር ልማት ፕሮጀክት ሳቢያ ታሪካዊ ይዘት ባለቸው ህንፃዎች ዙሪያ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል። ባለስልጣኑ በመግለጫው ህንፃዎች ሊፈርሱ የቻሉት ቅርስ ለመሆን የሚያስችላቸውን መስፈርት ባለሟሟላታቸው ነው ብሏል።

የቅርስ ጥናት እና ባለስልጣናት ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ በሚገኘው የልማት ፕሮጀክት ታሪካዊ እና ጥንታዊ የነበሩት ህንፃዎች በተለያዩ ዘፍፎች ቅርስ ለመባል የሚያስችላቸውን መስፈርቶች ባለሟሟላቸው እንደሆነ ገልፀዋል። አንድ ህንፃ የተገነባበት ዘመን፣ ውጫዊ እና ውስጣዊ ዲዛይኑ፣ ኪነ-ህንፃው፣ ታሪካዊ ዳራው፣ እና ሌሎች መስፈርቶችን ሟሟላት ሊኖርባቸው ይገባል ብለዋል።
በአራዳ ክፍለከተማ 147 ያህል ህንፃዎች በ2013/14 ዓ.ም በተካሄደ ምዝገባ በቅርስነት ተመዝግበው የነበረ ቢሆንም ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ግን የቅርስነት መስፈርት አያሟሉም ተብሏል።
በ-ሀሴት ኃይሉ
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












