አዲስ አበባ | መጋቢት 24፣ 2016| NBC ETHIOPIA- የዓለም የኦቲዝም ቀን ዛሬ መጋቢት 24፤ 2016 ይከበራል፡፡ እ.ኤ.አ 2007 በዓለም አቀፍ ደረጃ ፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኦቲዝም ቀን ሆኖ እንዲከበር ተወስኗል ፡፡

የዚህ ቀን መከበር ዋና አላማ ስለ ኦቲዝም ግንዛቤን ለማስጨበጥ እና የኦቲዝም ተጠቂዎችን በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን ተቀባይነት ለመጨመር ነው ተብሏል ።
ኦቲዝም ዘር፣ ቀለም ፣ ፆታ፣ ሃይማኖትን የመሰሳሉ ማኅበራዊና ተፈጥሯዊ ልዩነቶች አያግዱትም፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ሰው ኦቲስቲክ ልጅ የመውለድ ዕድል ሊኖረው ይችላል፡፡
ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር (ASD) ምልክቶቹ በልጅነት መታየት የሚጀምሩ ሲሆን በአብዛኛዉ ከ 3 ዓመት በፊት ሊከሰቱ እንደሚችሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ከዋናዋና ምልክቶቹ ውስጥ ሚከተሉት ይገኛሉ ፡-
-ጤናማ እና አስፈላጊ የሆኑ ማህበራዊ መስተጋብሮችን ማከናወን አለመቻል
-ንግግር ለመጀመር መዘግየት
-ተደጋጋሚ ባህሪያትን አና እንቅስቃሴን መተግበር
-የስሜት ህዋሳት ከመጠን በላይ መነቃቃት ወይም አለመነቃቃት
– የእንደን ነገር ድግግሞሽን አጥብቆ መፈልግ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
ኦቲዝም የሚድን ባይሆንም ቶሎ ከተደረሰበት እና የህክምና እርዳታ ማግኘት ከተቻለ ምልክቶቹን መቆጣጠር እና መቀነስ ይቻላል።
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
???? Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












