፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 24፣ 2016| NBC ETHIOPIA- እስራኤል በሶሪያ የኢራን ቆንጽላ ጽ/ቤት ላይ የሚሳዔል ጥቃት ፈጽማ የኢራንን የጦር አዛዦች ገደለች፡፡

ኢራን አጸፋዊ ምላሹን ጠብቁ ፤ቁርጠኛ እርምጃ እወስዳለሁም ብላለች ፡፡ የእስራኤል የሚሳዔል ጥቃት ሳይሆን አይቀርም የተባለውን አደገኛ ድርጊት የሩሲያ ፖቲከኞች ጭምር አውግዘውታል ፡፡
ለዚህም ነው ቀውሱ ዓለም አቀፋዊ ይሆናል የሚል ስጋት የተጋረጠው ፡፡ብርጋዴር ጀነራል መሀመድ ረዛ ዛሂዲ የኢራን ቁድስ እስላማዊ አብዮት ዘብ ሀይል አዛዥ እንዲሁም ምክትላቸው መሀመድ ሃዲ ሃጀሪሂሚ በሌሊቱ ጥቃት ህይወታቸውን አጥተዋል ፡፡
ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ እስራኤል በጉዳዩ ላይ ያለችው ነገር የለም ፡፡
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












