አዲስ አበባ | መጋቢት 23፣ 2016| NBC ETHIOPIA-የጉሮሮ ህመምን ከሚያስከትሉ ምክንያቶች መካከል በተለያዩ ተዋህስያን ኢንፌክሽን ምክንያት የሚመጡ እንደ ቶንሲል ህመም ያሉ በሽታዎች ዋነኞቹ ሲሆኑ አለርጂ፣ የጉሮሮ መድረቅ፣ በጣም ሙቅ የሆኑ ምግቦች ወይም መጠጦችን መውሰድ እና ድምፅን አብዝቶ መጠቀም የመሳሰሉ ምክንያቶች ደግሞ አነስተኛውን ድርሻ ይይዛሉ።

የቶንሲል ህመም
ቶንሲሎች በአፋችን የኃላ ክፍል ከእንጥል በግራና በቀኝ በኩል የሚገኙ እጢዎች ሲሆኑ ጥቅማቸውም ከምንመገባቸው ምግቦችና ከምንተነፍሰው አየር ጋር ተያይዘው ሊመጡ የሚችሉ ጎጂ ተዋህስያንን እንደመጀመሪያ መከላከያ መንገድ ሆኖ ማገልገል ነው፡፡ የእነኚህ ቶንሲሎች በኢንፌክሽን መጠቃት በተለምዶ “ቶንሲል” የምንለውን ህመም ያስከትላል፡፡ የቶንሲል በሽታ ማንኛውንም ሰው ሊያጠቃ ቢችልም አብዛኛውን ጊዜ በትምህርት መግቢያ እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ህፃናትን ያጠቃል፡፡
የቶንሲል በሽታ መንስኤው ምንድን ነው?
ቶንሲል በተለያዩ ምክንያቶች ሊቆጣ ቢችልም አብዛኛውን ጊዜ ግን በቫይረስ ወይም ባክቴሪያ ምክንያት በሚመጣ ኢንፌክሽን ይታመማል፡፡ አብዛኛው (25-45%) የሚሆነው የቶንሲል በሽታ በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ ሲሆን ባክቴሪያ በተለይም ግሩፕ ኤ ስትሬፕቶኮከስ (Group A streptococcus) የተባለው ባክቴሪያ ቀጣዩን ደረጃ ይይዛል፡፡ የቶንሲል በሽታ መተላለፊያ መንገዶች ከጉንፋን እና መሰል የመተንፈሻ አካላት በሽታ መተላለፊያ መንገዶች ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ እነዚህም በሽታው ያለበት ሰው በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ጊዜ በቅርበት መሆን፣ በቀጥታ ንክኪ ማለትም ንፁህ ባለሆኑ እጆች መጨባበጥ ወይም በተዋህስያኑ ከተበከሉ ግዑዝ ነገሮች ንክኪ ናቸው፡፡
መፍትሄው
-የቶንሲል ህመም በሚያጋጥም ጊዜ አቅራቢያ ወዳለ ጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል፡፡ የሚሰጠውም ህክምና ዓላማው
-አኪዩት ሪዩማቲክ ፊቨር (Acute rheumatic fever) ሳይከሰት በፊት በሽታው ያመጣውን ተዋህስ ማጥፋት- ይህም ፀረ-ተዋህስ መድሃኒቶችን በመስጠት ይታከማል (primary prevention)
አኪዩት ሪዩማቲክ ፊቨር (Acute rheumatic fever) ከተከሰተ ከእሱ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ምልክቶችን በማስታገሻና ሌሎች መድሃኒቶች ማከም
አኪዩት ሪዩማቲክ ፊቨር (Acute rheumatic fever) ተመልሶ እንዳይመጣና በልብ ቫልቮች ላይ የሚያመጣውን ጉዳት ለመቀነስ የሚደረግ መከላከያ (secondary prevention)- ይህ በሽታው በልብ ላይ ያለው ጉዳት ታይቶ ከ5 አመት እስከ እድሜ ልክ ድረስ በየወሩ በመርፌ መልክ በሚሰጥ መድሃኒት ይታከማል።

በመጨረሻም ቶንሲል በቀዶ ጥገና ስለማስወጣት
ቶንሲል በቀዶ ጥገና መወገድ የሚኖርበት ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው።
-ቶንሲል አብጦ ለመተንፈስ፣ ለመመገብ ወይም የእንቅልፍ መተኛት ችግር ካመጣ
-በመድሃኒት መዳን ያልቻለ መግል ቶንሲል ላይ ካለ
-በቋሚነት በቶንሲል ምክንያት የመጣ መጥፎ የአፍ ጠረን
-የካንሰርነት ጥርጣሬ ሲኖር
-በተደጋጋሚ ማለትም በ1 ዓመት ውስጥ 7 እና ከዛ በላይ፣ ለ2 ተከታታይ አመታት በዓመት ወስጥ 5 እና ከዛ በላይ፣ ለ3 ተከታታይ አመታት በዓመት ወስጥ 3 እና ከዛ በላይ ኢንፌክሽኖች ካሉ
-አብሮ ተያይዞ ሳል ወይም ጉንፋን መሰል ምልክቶች የማሳየት
-የቶንሲል መቅላት እና ማበጥ
-ቀለል ያለ ትኩሳት፣ ራስ ምታትና ብርድብርድ የማለት ምልክቶችን ያሳያል
-አንገት ላይ ያሉ እጢዎች (Lymph nodes) የማበጥ
-ከፍተኛ የሆነ ራስ ምታት፣ ትኩሳትና ብርድ ብርድ የማለት ምልክቶችን ያሳያል፡፡












