Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Health

የብረት ሳምባ

March 25, 2024
in Health
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አዲስ አበባ | መጋቢት 16፣ 2016| NBC ETHIOPIA -በዘመናችን ሰዎች በተለያዩ የጤና እክሎች ሲገጥሟቸው ሊያግዛቸው የሚችል ህክምና ያገኛሉ፡፡ ህክምና መፍትሄ መስጠት ሳይችል ሲቀር ደግሞ ቀሪ እድሜያቸውን በቴክኖሎጂ በመታገዝ የተለያዩ መሳሪያዎችን በመጠቀም ሲቀጥሉ ይስተዋላል፡፡

የመተንፈሻ አካላት ችግር ላለባቸው ሰዎች ተብለው የሚሰሩ ማሽኖች ደግሞ ቁጥራቸው በርከት ያለ ነው፡፡ ከነዚህም ውስጥ iron lung  ወይም የብረት ሳምባ አንዱ ነው፡፡  የመተንፈሻ ጡንቻዎችን መቆጣጠር ያቃታቸውን ታማሚዎች አተነፋፈስ ለማስተካከል የተሰራ ትልቅ አግድም ሲሊንደር መሰል መሳሪያ ነው፡፡ ይህ የብረት ሳንባ መሳሪያ ከፍተኛ እንክብካቤ በማድረግ ለብዙዎች በህይወት መቆየት መፍትሄ የሰጠ ነው፡፡

መሳሪያው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከከባድ የሳንባና የፖሊዮ ህመም ጋር እንዲኖሩ  አስችሏል፡፡ ከባድ የሳንባና መሰል የቫይረስ ኢንፌክሽን ሰውነትን በፍጥነት የሚያጠቃ ሲሆን በጥቂት ሰዓታት ውስጥ የመተንፈሻ ጡንቻዎች በማዳከም ወደ ሽባነት ሲያልፍም ለሞት ሊዳርግ ይችላል፡፡

ነገር ግን ይህን የብረት ሳንባ ህመምተኞች አየር እንዲያገኙ በማድረግ የተጎዳውን ሳንባ እንዲሰራና የግለሰቡ ህይወት ለዓመታት እንዲቀጥል ለማድረግ ያስችላል፡፡

ይህ የብረት ሳንባ የህጻናትን ህይወት ለመታደግ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው እ.ኤ.አ. በ1928 እንደሆነ ታሪክ ያስረዳና፡፡ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የፖሊዮ ወረርሽኝ በአለም ዙሪያ በተበከለ ምግብ እና ውሃ ተሰራጭቶ ነበር፡፡ እናም ከክትባት ባለፈ የብረት ሳንባ ከባድ ጉዳት ለደረሰባቸው ዋናው የሕክምና ዘዴ ሆኖ በማገልገል ለህክምናው ዘርፍ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ አሳይቷል፡፡

መሳሪያው በዋነኛነት የአየር ማናፈስ ስራን እንደሚሰራ ነው ባለሙያዎች የሚናገሩት፡፡ አየር ወደ ታካሚ ሳንባ ውስጥ በግፊት እንዲገባ በማድረግ ሳንባው ስራውን እንዲሰራ ያግዛል፡፡

ይህ ማሽን ሲነስ በአለም አቀፍ ደረጃ ስሙ የሚነሳው በቅርቡ ህይወቱን ያጣው ፖል አሌክሳንደር ነው፡፡  ፖል 70 አመታት ባሳየው ትዕግስትና እና ፅናት በአለም ዙሪያ ስሙ የገነነ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ፖል አሌክሳንደር በፖሊዮ ከተያዘ ከ70 ዓመታት በላይ በብረት ሳንባ ውስጥ ኖሯል። በብዙዎች በማህበራዊ ሚዲያ ፖሊዮ ፖል ተብሎ የሚጠራው ይህ ግለሰብ በ78 አመቱ ዳላስ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡

ታዲያ ዛሬ ምስጋና ለቴክኖሎጂ ይሁንና የቀደመው የብራት ሳምባ ወደ ዘመናዊ ICU ወይንም የፅኑ ህሙማን ክፍል ለመቀየር ችሏል፡፡ICU በፅኑ ለታመሙ ሰዎች ሕክምና እና ክትትል የሚሰጡ ልዩ የሆስፒታል ክፍሎች ናቸው። በልዩ የሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች የታቀፉ እና የተራቀቁ የክትትል መሳሪያዎችን ይይዛል፡፡ በተጨማሪም የትኛውን የአካል ክፍል ስራ ተክተው መስራት የሚችሉ በርካታ መሳሪያዎች በዚሁ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡

ቴክኖሎጂው የብረት ሳምባውን የመተንፈሻ አካል ድጋፍ መሰረት በማድረግ ለዘመናዊ የፅኑ ህሙማን ክፍሎች (ICU) እድገት ትልቅ ሚና መጫወቱን ቢቢሲ በዘገባው አትቷል፡፡ የብረት ሳምባው የተነደፈው ከጭንቅላት በስተቀር የታካሚውን አጠቃላይ አካል የሚሸፍን ባለመሆኑ አጠቃለይ የሰውነት ክፍልን ለመቆጣጠር እንዲያመች ተደርጎ አይሲዩ መሰራቱ ተጠቁሟል፡፡

በእርግጥ የብረት ሳምባው የመተንፈሻ አካልን ሽባ የሆኑ ታካሚዎች እንዲ ያድኑ በማድረግ የረጅም ጊዜ የመተንፈሻ አካላት ድጋፍ በመስጠት ውጤታማ መሆኑን ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡ ይህም ለመተንፈሻ አካላት ድጋፍ መስጠትና እና ዘመናዊ አይሲዩዎችን መመስረት መንገዱን ከፍቷል ነው የተባለው፡፡

ተመራማሪዎች እና የሕክምና ባለሙያዎች በብረት ሳምባው መርሆች ላይ በመደገፍ በአይሲዩ የአየር ማናፈሻ ዘዴዎችን በመመርመር ኦክሲጅንን ወደ ሳንባ የማድረስ ሂደት ሁለገብ እና ቀልጣፋ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ የብረት ሳምባዎች በአብዛኛው በዘመናዊ የአየር ማራገቢያ መሳሪያዎች እና በ(ICU) ውስጥ በሚገኙ ሌሎች የላቁ መሳሪያዎች ተተክተዋል፡፡

አይሲዩ ከመተንፈሻ አካል ባሻገር የበርካታ የአካል ክፍሎችን ስርዓትን ለመቆጣጠር የሚያግዝ መሳሪያ ነው፡፡ በዋናነት ልዩ እንክብካቤ እና ክትትል የሚሹ በጠና የታመሙ ታካሚዎችን ጤና ለማረጋጋት እና ለማሻሻል የሚያግዝ ዘመናዊ ክፍል መሆኑንም ቢቢሲ በዘገባው አካቷል፡፡

ለፅኑ ሕመምተኞች ልዩ እንክብካቤ ስለሚሰጡ የአይሲዩዎች መመስረት በጤና እንክብካቤ ውስጥ ትልቅ እድገት ሆኗል ተብሏል፡፡ አይሲዩ የላቁ የህክምና መሳሪያዎች፣ ከፍተኛ የሰለጠኑ የጤና አጠባበቅ ባለሙያዎች እና ሁለገብ የሆነ ክትትል፣ ድጋፍ እና ህክምና ስለሚደረግበት አስፈላጊነቱ ወሳኝ መሆኑን ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

ShareTweetShare
Previous Post

አጫጭር የውጭ መረጃዎች

Next Post

አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

Related Posts

⁨አዲስ ጥናት! _የማህበረሰብ ልማት ባለሞያ ዘላለም ይትባረክ! _NBC ቅዳሜ
Health

⁨አዲስ ጥናት! _የማህበረሰብ ልማት ባለሞያ ዘላለም ይትባረክ! _NBC ቅዳሜ

June 15, 2026
38
በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ መሠረተ ልማቶች ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ትልቅ አቅም እየሆኑ ነው
Health

በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ መሠረተ ልማቶች ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ትልቅ አቅም እየሆኑ ነው

June 4, 2026
24
⁨ሞት መድሃኒት አለዉ | ቆንጆ አለመሆኗ ሂዎቷን አመሰቃቅሎታል | ለራሳቸው መሆን የከበዳቸዉ ብዙ የህክምና ባለሙያውች አሉ | NBC ቅዳሜ
Health

⁨ሞት መድሃኒት አለዉ | ቆንጆ አለመሆኗ ሂዎቷን አመሰቃቅሎታል | ለራሳቸው መሆን የከበዳቸዉ ብዙ የህክምና ባለሙያውች አሉ | NBC ቅዳሜ

March 16, 2026
85
“ዳውን ሲንድረም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ስጦታ ነው!” | ውሎ በዲቦራ ፋውንዴሽን | በNBC እሁድ
Health

“ዳውን ሲንድረም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ስጦታ ነው!” | ውሎ በዲቦራ ፋውንዴሽን | በNBC እሁድ

February 17, 2026
48
ጥራቱ ያልጠበቀ ምርትን ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ
Health

ጥራቱ ያልጠበቀ ምርትን ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ

January 21, 2026
42
ወላጆች ስለ ልጆቻችችሁ ቶንሲል ግዴታ ማወቅ ያለባችሁ ነግሮች | ከታዋቂው የአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር | NBC ጤና
Health

ወላጆች ስለ ልጆቻችችሁ ቶንሲል ግዴታ ማወቅ ያለባችሁ ነግሮች | ከታዋቂው የአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር | NBC ጤና

August 25, 2025
89
Next Post
አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሰሞኑ አጋጥሞት ከነበረው ችግር ጋር ተያይዞ ከ801 ሚሊየን በላይ ገንዘብ ሊያጣ እንደነበረ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሰሞኑ አጋጥሞት ከነበረው ችግር ጋር ተያይዞ ከ801 ሚሊየን በላይ ገንዘብ ሊያጣ እንደነበረ አስታውቋል።

በጣሊያን አንድ ቤት በአንድ ዩሮ

በጣሊያን አንድ ቤት በአንድ ዩሮ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?