አዲስ አበባ | መጋቢት 13፣ 2016| NBC ETHIOPIA -የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፈው መጋቢት 7 ያጋጠመው ክስተት ከሲስተም ማሻሻያ ትግበራ ጋር የተያያዘ መሆኑን ማረጋገጡን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስታወቀ።
አስተዳደሩ ከባንኩና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አደረኩት ባለው የደህንነት ፍተሻና ምርመራ ባንኩ ያጋጠመው የሲስተም ችግር የሳይበር ጥቃት መሆኑን የሚያሳይ መረጃ እንዳላገኘ የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ ገልፀዋል።
ባንኩ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ለሚቃጡበት የሳይበር ጥቃቶች አስቀድሞ የመከላከል አቅም እንዳለው በፍተሻው ማረጋገጡን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።
ይልቁንም ባንኩ በሞባይል ሲስተሙ ላይ ያደረገው የማሻሻያ ስራ ለችግሩ መከሰት ምክንያት ናቸው ተብሏል።
በቀጣይ ተጨማሪ ምርመራዎችና የፎረንሲክ ስራዎችን በማድረግ ውጤቱን ለህዝብ እንደሚያሳውቅ አስተዳደሩ ገልጿል።
ህብረተሰቡ ከእዚህ ጋር በተያያዘ እየተናፈሰ ያለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን በመገንዘብ አገልግሎቱን ካለስጋት እንዲጠቀም ጥሪ ቀርቧል።
በ-መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












