፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 13፣ 2016| NBC ETHIOPIA -ከዛሬ 118 ዓመት በፊት መጋቢት 13፤1898 ዓ.ም ታሪክ ሲወሳ፤ ልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል (አባ ቃኘው) ከዚህ ዓለም የተለዩበት ቀን ነበር፡፡
ራስ መኮንን ወልደሚካኤል ግንቦት 1፤ 1844 ዓ.ም ጎላ ወረዳ ደረፎ ማርያም በሚባል ስፍራ ተወልደው እስከ 14 ዓመት ዕድሜያቸው ከአባታቸው ጋር ከኖሩ በኋላ የአጎታቸው የንጉሥ ኃይለመለኮት ልጅ ዳግማዊ ምኒልክ ገና የሸዋ ንጉሥ እንደነበሩ ወደርሳቸው ቤተ መንግስት መጥተው ባለሟል ሆነዋል።
በ1868 ዓ.ም ዕድሜያቸው 24 ዓመት ሲሆን ከወ/ሮ የሺእመቤት ጋር ተጋብተው ሐምሌ 16፤1884 ዓ.ም ንጉስ ሀይለስላሴን ወለዱ።
ልዑል ራስ መኮንን የዳግማዊ ምኒልክ ተወካይ ሆነው ሁለት ጊዜ የአውሮፓ ሀገራትን ጎብኝተዋል። ከጣሊያን ጋር በተደረገው ጦርነት ራስ መኮንን 15 ሺህ እግረኛ ወታደሮችን ይዘዉ ከምኒልክ እና ታላላቅ ጦር አዛዦች ጋርም ዘምተዋል።
በመጨረሻም ልዑል ራስ መኮንን መጋቢት 13 ፤ 1898 ዓ.ም አርፈው ሀረር ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እንደተቀበሩ ታሪክ ይዘክራል ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












