፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 06፣ 2016| NBC ETHIOPIA -ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቱኒዚያ በተካሄደው የሁዋዌ የአይሲቲ ክፍለ አህጉራዊ ፍጻሜ ውድድር ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል።
ውድድር ከየካቲት 28 እስከ መጋቢት 1 ቀን 2016 ዓ.ም በቱኒዚያ ተካሂዶ የነበረ ሲሆን ኢትዮጵያን ወክለው ከተወዳደሩት መካከል በኮምፒውቲንግ ትራክ (Computing Truck) የተወዳደሩት የሦስት ተማሪዎች ቡድን ሞሮኮ እና ቱኒዚያን ተከትለው ሶስተኛ ደረጃን አግኝተዋል።
ውድድር ላይ ከኢትዮጵያ፣ ማሊ፣ ካሜሩን፣ ሴኔጋል፣ አልጄሪያ፣ ቱኒዚያ፣ ሊቢያ፣ ግብፅ እና ሞሮኮ የተወጣጡ 90 ተማሪዎች በተለያዩ ዘርፎች ተሳትፈዋል።
አሸናፊዎች በ2024 በቻይና በሚካሄደው እና ከ500 ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ ከ20 ሺህ በላይ ተማሪዎች በሚሳተፉበት የመጨረሻው ምዕራፍ ውድድር ላይ የመሳተፍ ዕድል ይኖራቸዋል ተብሏል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












