፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 04፣ 2016| NBC ETHIOPIA -ረሐብ በጋዛ ምድር እንደጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ ውሏል ሲል አውሮፓ ህብረት ዕወቁልኝ አለ፡፡
የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል እርዳታ ወደ ፍልስጤም አለመግባቱን ሰው ሰራሽ ቀውስ በጋዛ ምድር ብለውታል፡፡
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በደቡባዊ ጋዛ ጥቃታቸውን አጣናክረው በቀጠሉበት ሰዓት ነው ቦሬል ይህን ያሉት፡፡
የእርዳታ ሰራተኞች እስራኤል በጋዛ ያደረገችው የእንቅስቃሴ ገደብ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ ተግዳሮት ፈጥሮብናል ይላሉ፡፡
አሁን ላይ ለጋዛውያን ሰብዓዊ ድጋፍ በባህር እና በአየር ላይ አማራጭም ሆኗል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv











