፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 04፣ 2016| NBC ETHIOPIA – የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አገራቸው ለኒውክሌር ጦርነት ዝግጁ መሆኗን ዓለም ትወቅ አሉ፡፡

ፑቲን የሩሲያን ኒውክሌር ጦር መሳሪያ አቅም ማሳደግ ላይ ናቸው፡፡ሞስኮ ከ 6 ሺህ በላይ የኑክሌር አረር ጫፍ ጦር መሳሪያዎችን በመታጠቅ በዓለም ቁጥር አንድ ላይ ትገኛለች፡፡
ፑቲን ምዕራባውያንን ለመገዳደርም ሆነ ለሚገጥማቸው ጦርነት ኒውክሌርን እንደብቸኛ አማራጭ እየወሰዱ ነው በሚል ቢተቹም የቁርጥ ቀን አማራጫችን ኒውክሌር ነው ይሉታል ፡፡

በሩሲያ አገርነት ላይ ስጋት የሚጭር ነገር ካለ ሞስኮ ኒውክሌር ለመጠቀም ዝግጁ ናትም ብለዋል ፑቲን ፡፡
ከወታደራዊ እሳቤ አንጻር የሩሲያ ጦር ለኒውክሌር ፍጥጫ ዝግጁነቱንም ፑቲን በተቀረጸ ቃለ መጠይቃቸው አሳውቀዋል ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












