፨ ፨ ፨ ፨ ፨
ኬንያ ወደ ሄይቲ 1 ሺህ የፖሊስ ዓባላት የመላክ ውጥኗን ማዝግየቷን አስታወቀች፡፡የሄይቲው ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሪየል ሄንሪ ከስልጣን እንደሚነሱ ማሳወቃቸውን ተከትሎ ነው ኬንያ ይህን ያለችው፡፡
ከኬኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አገኘሁት ያለውን መረጃ ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ እንደዘገበው ናይሮቢ አዲስ ህገ መንግስታዊ ባለስልጣን በሄይቲ እስኪመሰረት ጉዳዩን በይደር ይዛዋለች ፡፡
አገሪቱ 1 ሺህ የፖሊስ ዓባላትን ለሄይቲ ለመላክ ወስና ነበር፡፡በፖርት ኦው ፕሪንስ ወንበዴዎች ለዴሞክራሲ አደጋ መደቀናቸውን ተከትሎ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ስልጣናቸውን ከለቀቁት የሄይቲው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተስማምተው ነበር፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












