አዲስ አበባ | የካቲት 29፣ 2016| NBC ETHIOPIA -ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሴቶች ቀን ሲከበር የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በፌደራል መንግስትና በከተማ አስተዳደር አማካኝነት ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል።

የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ቁልፍ የዉሳኔ ሰጪነት ቦታ ላይ መቀመጣቸውን ገልፀዋል። በርካታ ስራዎችን ቢሰሩም አሁንም የሴቶችን ተሳትፎ በፖለቲካ ፣በኢኮኖሚ እንዲሁም በማህበራዊ ጉዳዮች ለማጠናከር በርካታ ስራዎች እንደሚፈልግ ተናግረዋል።
ከተማ አስተዳድሩም የሴቶችን ተሳትፎ ለማጎልበት በተለይም በወሲብ ንግድ የተሰማሩትን ሴቶች ስልጠና በመስጠት ስራ እንዲያገኙ የሚያስችል የሴቶች ተሃድሶና ልህቀት ማዕከል ተገንብቶ ለምረቃ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።
በ-ሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












