፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡
አዲስ አበባ | የካቲት 26፣ 2016| NBC ETHIOPIA -በስኮትላንድ ግላስኮው በተካሄደው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የላቀ ውጤት ያስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ።
-በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በኋላ በክለብ ደረጃ ሃዋሳ ከተማ፣ ፋሲል ከነማና አዳማ ከተማ የስነ ምግባር ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡
-የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች ሙልጌታ ወ/ጊዮርጊስ ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቶ ወደ ሻሸመኔ ከተማ ክለብ መዘዋወሩ ተገልጿል።
-በአውሮፓ ቻምየንስ ሊግ የ16ቱ ዙር የመልስ ጨዋታ ባየር ሙኒክ ከላዚዮ፣ ሪያል ሶሴይዳድ ከፒ ኤስ ጂ ምሽቱን ይጫወታሉ፡፡
-የፈረንሳይ ሊግ ከቀጣይ የውድድር ዓመት ጀምሮ ከ “Uber Eats” ጋር ያለውን የስያሜ መብት ውል አቋርጦ ከማክዶናልድ ጋር እንደሚሰራ ተነግሯል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












