የመጀመሪያ ደረጃ መከላከል (primary level of prevention)
እነዚህ መጀመሪያ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር በሽታ ከመከሰቱ በፊት መወሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች ያጠቃልላሉ።

የሥነ ባሕርይ ለውጥ (behavioural):- እንደሚታወቀው የማህፀን ጫፍ ካንሰር 90% በላይ የሚሆነው የሚተላለፈው Human Papilloma Virus(HPV) በተሰኙ የአባላዘር በሽታ አምጪ ቫይረሶች ስለሆነ አጋላጭ የግብረ ስጋ ግንኙነቶችን ማስወገድ ትልቁ አንኳር ጉዳይ ነው። ይህውም 3ቱ የ”መ” ሕጎች ወይንም “ABCs” የምንላቸውን መከላከያ መንገዶች ያጠቃልላል።
✔️ መታቀብ (Abstainence)- በተለይ ያለዕድሜ ጋብቻ፣ ከ16 ዓመት በፊት የሚደረግ ግንኙነት እንዲሁም በእድሜ ከገፉ ወንዶች ጋር የሚኖር ግንኙነት የተጋላጭነት ዕድልን የሚጨምሩ ናቸው።
✔️ መወሰን (Be faithful)- በታማኝነት ላይ የተመሰረተ የመጀመሪያውን አንስቶ አንድ ባል ለአንዲት ሚስት ብቻ የሚኖር ግንኙነት ከሆነ ተጋላጭነትን በእጅጉ ይቀንሰዋል።
????መጠቀም (Condom):- ይህም መንገድ እንኳ ከላይ የጠቀስናቸው መንገዶች ካልተሳኩ ይመከራል ነገር ግን 100% ይከላከላል ማለት አይደለም።
መከትብ (vaccination):- ሳይንስ ከደረሰባቸውና ካንሰርን በክትባት መልክ መከላከያ መንገዶች ያሉት የማህፀን ጫፍ ካንሰር ዋነኛው ሲሆን ክትባቱ ግን የሚሰጠው ከ9-14 ዓመት ለሆናቸውና ግንኙነት ላልጀመሩ ልጃገረዶች እንዲሆን ይመከራል።
የክትባቱ ትልቁ ጥቅም የHPV ኢንፌክሽን እንዳያጠቃና ኤንፌክሽኑ ገና ቀድሞ ወደ ካንሰርነት ደረጃ እንዳይቀር እንጂ በካንሰርነት ደረጃ ላይ ለደረሰ ሕመም ምንም ፋይዳ የለውም፤ HPV positive የሆነውን ወደ HPV negative በፍፁም አይቀየርም።
የኤችፒቪ ቫይረስ (HPV) መከላከያ ክትባት የተለያዩ አይነቶች ያሉት ሲሆን በእኛ ሃገርም እየተሰጠ ይገኛል። የመከላከል ብቃቱ ደግሞ ከ80-90% በላይ ውጤታማ ይደርሳል።
ሁለተኛ ደረጃ መከላከል (Secondary level of prevention)

ይሄኛው ደግሞ ቅደመ ካንሰር የምርመራ ሂደት (precancerous lesions screening and treatment) ተብሎ የሚጠራም ሲሆን ዋነኛ ዓላማው ደግሞ አንድ የኤችፒቪ ቫይረስ (HPV) ኢንፌክሽን ወደ ካንሰርነት ደረጃ ለመሸጋገር በትንሹ 10-15 ሊወስድ ይችላልና በዚህ መካከል የሚታዩትን ለውጦች አስከፊ ደረጃዎች ላይ ሳይደርስ የሚደረጉ ምርመራዎችን እና ወዲያውኑም የሚወሰዱትን የሕክምና እርምጃዎችን ያጠቃልላል።ይህ መርህ ደግሞ “ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መታከም” የሚል አንድምታ አለው።
በዚህም መሰረት የተለያዩ ምርመራዎችን ማሰራትና በዚሁ ተነስቶ የሚወሰዱ ሕክምናዎች ያሉት ሲሆን በእኛም ሀገር እየተሰራበት ይገኛል።
ለማየት ያክል:-
የፓፕ ምርመራ (pap smear):- ይህ የምርመራ አይነት ከማህፀን ጫፍ (cervix) ላይ ናሙና በመውሰድ በአጉሊ መነጽር (Microscope) በመታገዝ የሥነደዌ ሕክምና እስፔሻሊስት(pathologist) የካንሰር ሴሎች አለመኖራቸውን የሚያረጋግጥበት መንገድ ሲሆን ከ21-65 ዓመት ላሉ ሴቶች በየአምስት ዓመቱ ይሰራል። በደማቸው ውስጥ ኤችአይቪ ላለባቸው ግን የግብረስጋ ግንኙነት ከጀመሩ አንስቶ በየዓመቱ ሊደረግ ይችላል።
ይህ ምርመራ በሀገራችን የሚሰራ ቢሆንም ከዋጋው ወደድ ማለት እና የዘርፉን ባለሙያዎችንም ከማስፈለጉም አንፃር በሁሉም ቦታ አይገኝም።
VIA/VILI ( visual inspection with asectic acid or lugols iodine)፦ እነኚህ የምርመራ አይነቶች ደግሞ በቀላሉ የሚገኙና እምብዛም ያልተወሳሰቡ ስለሆኑ በየትኛውም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ጨምሮ በቀላሉ የሚገኙ ሲሆን ችግር ከተገኘ ወዲያውኑ ማየት አብሮ ማከም በሚል መርህ ይከወናሉ።ይሄ ደግሞ የሚሰራላቸው ሴቶች ከ30-49 ዓመት ያሉ ሴቶች ላይ የሚሰራ ነው፡፡
የሕክምናው አይነቶች የተለያዩ አይነቶች ናቸው:- በቅዝቃዜ (cryotherapy)፣ ሙቀት (laser ablation) እንዲሁም ደግሞ በቀዶ ሕክምና ቆርጦ ማውጣት (LEEP, conization,… )የመሳሰሉትን ያጠቃልላል።
ሦስተኛ ደረጃ መከላከል (Tertiary Level of prevention)

ይሄኛው ደረጃ ደግሞ በሽታው የካንሰር ደረጃ ከደረሰ በኋላ የሚወሰዱትን እርምጃዎች ማለትም FIGO-Staging በተሰኘ የሕክምና የማህፀን ጫፍ ካንሰር ክፍፍልን መሰረት በማድረግ ወደ አራት ዋና ክፍሎች (stage-I, II, III, IV) ተብሎ ከተሰጠው በኋላ እንደገና ንዑስ ክፍሎችን በ a,b c እየተደረገ በዘርፉ ባለሙያዎች የሚወሰን ሆኖ እንደ የሁኔታው በቀዶ ሕክምና (surgery)፣ በጨረር (radiation therapy)፣ በካንሰር መድኃኒት (chemotherapy) አማካኝነት ለየብቻ ወይንም ሁሉንም በአንድ ጊዜ እየተደረገ ከደረጃ (Stage) 1-3 ያሉት የሚታከሙበት መንገድ እንደየሁኔታው ያለ ሲሆን ለመጨረሻው ደረጃ (stage-4) ከደረሰ ግን የድጋፍና በርህራሄ ማገዝ ሕክምና (supportive and palliative Care) ሕክምና ዘዴዎችን እንዲያገኙ ይደረጋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












