፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡
አዲስ አበባ | የካቲት 25፣ 2016| NBC ETHIOPIA -በ19ኛው የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም አምስተኛ በመሆን አጠናቃለች።
በስኮትላንድ ግላስጎ ሲካሄድ የነበረው 19ኛው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ትናንት ሌሊት ተጠናቋል።
በውድድሩ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ከ650 በላይ አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን ኢትዮጵያም በ800 ሜትር፣ በ1500 ሜትር እና በ3000 ሜትር ርቀቶች በ8 ሴቶች እና በ5 ወንዶች በድምሩ በ13 አትሌቶች ተሳትፋለች ፡፡
በዚህ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሁለት ወርቅ በአንድ ነሀስ እና በአንድ ብር በአጠቃላይ በአራት ሜዳሊያዎች ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም አምስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












