Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

                         ራስ መንገሻ ዮሐንስ

March 2, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አንዳንድ ጊዜ ታሪክ በቤተ መፅሐፍት መደርደሪያ ላይ ከተደረደሩ መዛግብትና ሰነዶች ውጪ ይገኛል፡፡ በምንዘዋወርበት ጐዳና፣ በሕንፃዎች፣ በሐውልቶች እና አደባባዮች ላይ ታሪክን ሰፍሮ ልናገኘው እንችላለን፡፡

በጣሊያን ሮም ከተማ ከሚገኘው ማዕከላዊ የባቡር ጣቢያ የሚወጡ መንገደኞች ወይም ሀገር ጐብኚዎች መጀመሪያ የሚያገኙት “ፒያሳ ዲ ቺንኩዊቼንቶ” ወይንም “የአምስት መቶዎቹ አደባባይ” እየተባለ የሚጠራውን ቦታ ነው፡፡ የተወሰኑት መንገደኞች ታክሲዎች እና ሱቅ-በደረቴዎች በሚፈጥሩት ግርግር ምክንያት ለአደባባዩ ምንም ትኩረት ሳይሰጡ አልፈውት ሊሄዱ ይችላሉ፡፡

አንዳንዶቹ ይህ ቦታ የሀገሪቱ ዜጎች በኩራት የሚያወሩለት በ1500 ጣሊያን ደርሳበት የነበረው የሕዳሴ ዘመን ትቶት ያለፈው ቅርስ እንደሆነ ሊገምቱ ይችላሉ፡፡ በመኪና ፍቅር የተለከፉ ሰዎች “ፊያት ቼንኩዊቼንቶ” ከሚለው መጠሪያ ጋር ግንኙነት ያለው መስሏቸው የሀገሪቱን የመኪና ኢንዱስትሪ ወደ ትልቅ ደረጃ ስላደረሰው የፊያት ኩባንያ ቢያስቡ አይፈረድባቸውም፡፡ “ፒያሳ ዲ ቺንኩዊቼንቶ” የኢጣሊያ ጦር በአፍሪካ ምድር ዶጋሊ በተባለ ቦታ ታላቅ ወታደራዊ ሽንፈት ባጋጠመው ጊዜ ለሞቱ አምስት መቶ የኢጣሊያ ወታደሮች መታሰቢያ የተሰራ አደባባይ ነው፡፡

እነዚህ “ዶጋሊ” በተባለ ስፍራ በተደረገ ጦርነት የወደቁ የኢጣሊያ ወታደሮች መስዋዕት የሆኑበት ምክንያት የኦቶማን ቱርክ ኢምፓየር ከሱሊማን ቀዳማዊ የስልጣን ዘመን አንስቶ (ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ) እስከ 18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ለሶስት መቶ አመታት የዘለቀውን በምዕራብ የቀይ ባህር ዳርቻ ከጅቡቲ ባህር ወሰን አንስቶ እስከ ሱዳን የባህር ዳርቻዎችን የሚያካልል ሰፊ ግዛቱን ለማስተዳደር የሚያስችል አቅም በማጣቱ ጣሊያን የተፈጠረውን ክፍተት ለመጠቀም መወሰኗ ነው።

ከጣሊያን የዶጋሊ ድል በኋላ የመጣው የአደዋ ጦርነት የወለደው የአደዋ ድል ነበር። የአደዋ ድል የተገኘው ኢትዮጵያውያን በጋራ የመሩበትና የተዋጉበት ታሪካዊ ጦርነት መሆኑ ይነገራል። የአደዋ ጦርነትን ከመሩት 12  አዛዦች አንዱ ራስ መንገሻ  ዮሐንስ አንዱ ናቸው።

ራስ መንገሻ ዮሐንስ የትግራይ አስተዳዳሪ ነበሩ። የተወለዱት በ1857 ዓ.ም. ትግራይ ውስጥ ነው።  የንጉሥ ዮሐንስ አራተኛ ልጅ ሲሆኑ፤ እናታቸው  ወለት ተክለ ሀይማኖት ይባላሉ። ራስ አርአያ  ኃይለስላሴ ዮሐንስ የራስ መንገሻ ዮሐንስ ታናሽ ወንድም ናቸው።

ራስ መንገሻ ዮሐንስ  የንጉሥ ዩሐንስ የወንድም ልጅ በመሆን ያደጉ ናቸው። ራስ መንገሻ የንጉሥ ዮሐንስ ልጅ መሆናቸው የተነገረው በመተማ ጦርነት 1882  መሞታቸውን ተከትሎ ነበር። ራስ መንገሻ ዮሐንስ በአደዋ ጦርነት የጣሊያንን ወረራ ከቀለበሱ አመራሮች አንዱ ናቸው።

ራስ መንገሻ ዮሐንስ የአጼ ዩሐንስ ወታደራዊ አዛዥ ጀነራል ራስ አሉላ  ጠንካራ የወታደራዊ እና የፖለቲካ  ድጋፍ  ነበራቸው። በተጨማሪም ራስ መንገሻ ዮሐንስ  የዩሐንስ 4ኛ በቁጥር የጦር መሳሪያዎች እና ወታደሮች ወራሽ  በመሆናቸው አቅም ጨምሮላቸዋል።

አፄ ዮሐንስ እንደሞቱ እና አፄ ምኒልክ የንጉሠ-ነገስትነቱን ቦታ እንደያዙ ራስ መንገሻ የትግራይ አገረ ገዥነት ተሰጣቸው፡፡ ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከአጼ ምንሊክ ጋር የተወሰነ ቁርሾ ነበራቸው። ጣሊያን ሁለቱ ያላቸውን ልዩነት ለመጠቀም ብዙ ሞክራለች። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከአጼ ምንሊክ ላይ እንዲያምጹ ስትሞክር ነበር።

የአደዋ ጦርነት ሲከሰት ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከአጼ ምንሊክ ጋር ያላቸውን ልዩነት ወደ ጎን በመተው በሀገራቸው የመጣውን ጠላት በጋራ ለመመከት  ተንቀሳቀሰዋል። ራስ መንገሻ ዮሐንስ በአድዋ ዘመቻ ያሰለፉት የሠራዊት ብዛት 12000 ነበር፡፡

ከአድዋ ጦርነት በፊትም ሆነ በኋላ ጣሊያኖች በስተጀርባ ሆነው በንጉሠ-ነገሥቱ ላይ እንዲያምፁ ይገፏፏቸው ነበር፡፡ ምፅዋ ላይ የነበሩት ጣሊያኖች ራስ መንገሻን እንዲያምፁ የሚያደጉርት የስልጣንን ጉዳይ እያነሱ ነበር፡፡ ራስ መንገሻ የጣሊያን ውትወታ አሸንፏቸው በአፄ ምኒልክ ላይ ሸፈቱ፡፡

አፄ ምኒልክም ከራስ መኮንን ጋር ከራስ (በኋላ ንጉሥ) ሚካኤልን፣ ዋግሹም ጓንጉልን እና ደጃዝማች (በኋላ ራስ) አባተን አጋዥ አድርገው “አውቆ እጁን ቢሰጥ ይዛችሁት፤ እምቢ ካለ ውጉት” ብለው ወደ ትግራይ ላኳቸው፡፡ እቴጌ ጣይቱም ደብዳቤ ፅፈው ላኩለት፡፡

ደብዳቤው ቢደርሳቸውም ራስ መንገሻ በሰላም ሊመለሱ ባለመፍቀዳቸው በልዑል ራስ መኮንን የሚመራው ጦር ወደ እደጋ ሐሙስ በመሄድ ከበባ አደረገ፡፡

ጦርነቱ ከመደረጉ በፊትም ራስ መኮንን እና የአባታቸው የአፄ ዮሐንስ የክርስትና ልጅ ከሆኑት ከዚያን ጊዜው ራስ ሚካኤል በሰላም እንዲገቡ በሚል የምክር ቃል ተላከባቸው፡፡

ለውጊያ መዘጋጀታቸው ስለተሰማ ይገኙበት ከነበረው ሥፍራ በስተጀርባ በአጋሜ በኩል አራት ሺህ ባለጠመንጃ ጦር ዘልቆ ሄዶ ጦርነት ገጠማቸው፡፡ የራስ መንገሻም ጦርም ክፉኛ በመጎዳቱ እጃቸውን ሰጡ፡፡ ራስ መንገሻም በአንኮበር አምባ ታስረው ተቀመጡ፡፡

በትዳር ሕይወታቸው የእቴጌ ጣይቱ የወንድም ልጅ ከሆኑት ከጎንደሯ እመቤት ከወ/ሮ ከፋይ ወሌ ብጡል ተጋብተው ወ/ሮ አስቴር መንገሻን፣ ወ/ሮ አልማዝ መንገሻንና ወ/ሮ ብርሃኔ መንገሻን ወልደዋል፡፡

በአንኮበር አምባ ታስረው ባሉበት ወቅት እቴጌ ጣይቱ በክብር ያጋቧቸውን የወንድማቸውን ልጅ ወ/ሮ ከፋይን አፋተው መልሰው ለራስ ናደው ዳሩላቸው፡፡ ራስ መንገሻ እስከ እድሜያቸው ፍፃሜ በእስር ላይ ቆይተው ህዳር 6/1899 ዓ.ም. እዚያው አንኮበር አምባ ላይ እንዳሉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

የአድዋ ድል እንደ ራስ መንገሻ ዩሃንስ ባሉ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የጦር መሪዎች እየተመራ ነጠላትን ጦር ድል አድርጓል። ድሉ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላ አፍሪካ ብሎም የጥቁር ህዝቦች ቀንዲል ሆኖ ዘላለም ይዘከራል።

በ-እስክንድር ከበደ

ShareTweetShare
Previous Post

ራስ አሉላ አባ ነጋ

Next Post

በአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም አምስተኛ በመሆን አጠናቀቀች

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
በአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም አምስተኛ በመሆን አጠናቀቀች

በአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም አምስተኛ በመሆን አጠናቀቀች

አጫጭር የውጭ መረጃዎች

አጫጭር የውጭ መረጃዎች

አጫጭር የሃገር ውስጥ መረጃዎች

አጫጭር የሃገር ውስጥ መረጃዎች

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?