አዲስ አበባ | የካቲት 23፣ 2016| NBC ETHIOPIA -128ኛው የአድዋ ድል በዐል በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እየተከበረ ይገኛል።
በክብረ በዐሉ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ሊወሯት እና ሊያጠቋት የመጡ ጠላቶቿን በድል መልሳለች ብለዋል።
የአድዋ ድል በዐል እስከዛሬ ለመታሰቢያነት ያህል ይከበር የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ በዚህ ትውልድ ድሉን የሚመጥን እና ኢትዮጵዉያንን የሚያሰባስብ መታሰቢያ መገንባቱን ገልፀው በግንባታው ለተሳተፋት ምስጋና አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ አሁንም እየሄደችበት ያለውን ፈጣን የልማት ጉዞ ሊያደናቅፋ የሚጥሩ አንዳንድ አካላት ቢኖሩም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ቀን ከሌት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በ-የአብስራ ሚሊዮን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












