አዲስ አበባ | የካቲት 21፣ 2016| NBC ETHIOPIA -“የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ተዓማኒነት ግብረ ሃይል የትብብርና ቅንጅት የመግባቢያ ስምምነት ቁ.01/2016” የሚል ስያሜ የተሰጠው አንደኛው ስምምነት በዘርፉ ተሳታፊ በሆኑ ባለድርሻ አካላት መካከል ቀልጣፋ ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት እንደሚያግዝ ተነግሯል።
ስምምነቱ በፍትህ ሚኒስቴር፣ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት መካከል የተፈረመ ነው።
የካፒታል ገበያውን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ያለመው ሌላኛው ስምምነት በየኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት መካከል ተፈርሟል።
ስምምነቱ ከሳይበር ደህንነት ጋር የተያያዙ የቴክኖሎጂ ድጋፎችን ያካተተ ሲሆን ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በካፒታል ገበያው ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመቆጣጠርና የቁጥጥር ማዕቀፉን ለማሳደግ ያግዛል ተብሏል።
ስምምነቶቹ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ያሉበትን ችግሮች ለመቅረፍ እንደሚያግዙ ተስፋ ተጥሎባቸዋል።
በ-መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












