አዲስ አበባ | የካቲት 12፣ 2016| NBC ETHIOPIA -የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በ37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ኢትዮጵያ ከፍ ያለችበት፣ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ የሚያስችሉ ሥራዎች የተሰሩበትና በስኬት የተጠናቀቀ መሆኑን አስታወቀ።
-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የድርሻ ገበያ እና ልውውጥ (ስቶክ ማርኬት ኤንድ ኤክስቼንጅ) መጀመር ኢትዮጵያ የእድገት ትልሟ እውን እንዲሆን አዳዲስ ካፒታል በመሳብ ጨዋታ ቀያሪ መሆኑን ገልጸዋል።
-አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሙዌኔ ዲቱ ዩኒቨርሲቲ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
-የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ዋና ዳይሬክተር ገርድ ሙለር ጋር በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ዙሪያ ተወያዩ፡፡
-በኢትዮጵያ ያለውን የግብርና አቅም ለማጎልበት እንደሚሠራ የአፍሪካ የሥጋት አስተዳደር ግሩፕ አስታወቀ፡፡
-የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት 3 ነጥብ 25 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ሙሊት ሥራ መከናወኑ ተገለጸ፡፡
-የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ከአሜሪካ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።
-87ኛው የየካቲት 12 መታሰቢያ በአዲስ አበባ ሥድስት ኪሎ የሰማዕታት ሐውልት ተከበረ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












