አዲስ አበባ | የካቲት 05፣ 2016| NBC ETHIOPIA – የሰቆጣ ቃልኪዳን በኢትዮጵያ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ መተግበር የጀመረ ሲሆን በሀገሪቷ የነበረው የህፃናት መቀንጨር ምጣኔን ወደ 39በመቶ እንዲቀንስ ማድረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የጤና ሚኒስቴር ከሪዛልት ፎር ዴቬሎፕመንት ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር የሰቆጣ ቃል ኪዳን የማስፋፋት እና የማስፋት ምዕራፍ የሀብት ማሰባሰብ እቅድ በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል።
ቃል ኪዲኑ የኢትዮጵያ መንግስት በ2030 እ.ኤ.አ ከ2 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን የመቀንጨር ችግርን ለመቅረፍ በማለም እየተሰራ ይገኛል።
መንግስት የዜጎችን የምግብ እና ስርዓተ ምግብ ለማሻሻል የማስፋፋት ምዕራፉን ትግበራ ለማሳደግ ከ240 ወረዳዎች ወደ 700 ለማሳደግ ወደ ስራ መገባቱን የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ በመድረኩ ገልፀዋል። ይህንንም ከግብ ለማድረስ 146 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።


በመድረኩ የጤና ሚኒስቴር አመራሮችና ስራ አስፈጻሚዎች፤ ጤና ቢሮ ሃላፊዎች ፤ የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ተወካይ ፤ አጋር ድርጅቶች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በ-ሀሴት ኃይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












