አዲስ አበባ | የካቲት 05፣ 2016| NBC ETHIOPIA – ለሦስተኛ ጊዜ ሆስፒታል የገቡት የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን ለሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ጥምረት ወይም ኔቶ የሚያደርጉትን የስብሰባ ጉዞ መሰረዛቸው ታውቋል፡፡

ሚኒስትሩ በቤልጂየም ብራስልስ በዩክሬን ጉዳይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የሚካሄደውን ስብሰባ ይመራሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር።
ኦስቲን ማክሰኞ ወደ ሥራቸው እንደሚመለሱ ፔንታገን ገልጾ የነበረ ሲሆን ፤ ለጊዜው ግን ሀላፊነታቸው ለምክትላቸው እንዲተላለፍ ተደርጓል ተብሏል። ዘገባው የቢቢሲ ነው
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












