አዲስ አበባ | የካቲት 01፤ 2016| NBC ETHIOPIA – የካቲት 03 ቀን 2016 ዓ.ም የሚካሄደውን የዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም የምረቃ ስነ-ስርዓትን ተከትሎ በዕለቱ ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደርገዋል፡፡
የዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም በደማቅ ስነ-ስርአት የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም እንግዶች እና የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይመረቃል።
የምረቃ በዓሉን ተከትሎም በዕለቱ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑም የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት:-
-ከአፍንጮ በር ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን፣
-ከሰሜን ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን፣ከዮሃንስ ቤተ ክርስቲያን ወደ አቡነ ጴጥሮስ፣
-ከአራት መንታ ወደ ጅንአድ፣
-ከይርጋ ሃይሌ የገበያ ማዕከል ወደ አቡነ ጴጥሮስ፣
-ከሃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ወደ ሱማሌ ተራ ፣
-ከሱማሌ ተራ ወደ ኤሊያና ሆቴል(ባንኮዲሮማ) መስቀለኛ፣
-ከተክለ ሃይማኖት አደባባይ ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ
– ከሀገር አስተዳደር መብራት (ኢሚግሬሽን) ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ፣
-ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ፣
-ከአሮጌው ቄራ ወደ ባንኮ ዲሮማ መብራት፣
-ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ፣
-ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ፣
-ከመቅደላ ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን፣
-ከቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ወደ ቴሌ እና ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደሚገኘው አደባባይ የሚወስዱት መንገዶች በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ ነው የተባለው፡፡
ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች ይህንን ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና የትራፊክ ፖሊሶች በሚጠቁሟቸውን አማራጭ አቅጣጫዎችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












