አዲስ አበባ | የካቲት 01፤ 2016| NBC ETHIOPIA – የአጭር ርቀት ንግስቷ ሸሊ- አን ፍሬሰር-ፕራይስ ከ2024 የፓሪስ ኦሊምፒክ በኋላ ጡረታ እንደምትወጣ አስታውቃለች።

ጃማይካዊት የ3 ጊዜያት የኦሊምፒክ አሸናፊ ጡረታ የመውጣት ዉሳኔ ላይ ለመድረሷ ያቀረበችው አመክንዮ “ለቤተሰቦቼ ጊዜ መስጠት አለብኝ” የሚል ነው።
“ከእንቅልፌ ተነስቼ ወደ ልምምድ የምሄድበት ልማዴ የሚያበቃበት ጊዜው ደርሷል” ብላለች።
ከባለቤቷ ጋር በ2008 የቤጂንግ ኦሊምፒክ ከማሸነፏ በፊት ጀምሮ አብረው ይኖሩ እንደነበርና በህይወቷ ትልቅ መስዋዕትነት እንደከፈለላት በማስገንዘብ፤ ከአሁን በኋላ ግን ለእርሱና ለልጇ ጊዜ መስጠት ግድ እንደሚላት ለኢሴንስ ዶት ኮም ተናግራለች።
የ37 ዓመቷ ፍሬሰር – ፕራይስ በ2008 የቤጂንግና 2012 የለንደን ኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ በ100 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፏ ይታወሳል።
በ2020 የቶክዮ ኦሊምፒክ በ4× 100 ዱላ ቅብብል ውድድርም እንዲሁ። በዚህ መድረክ ከዚህ በተጨማሪ 4 የብርና 2 የነሀስ ሜዳሊያዎችን አሳክታለች።
ከአጠቃላይ 10 ዓለም አቀፍ ሽልማቶቿ 3ቱ በ2017 የመጀመሪያ ልጇን ወልዳ ከተመለሰች በኋላ ያሸነፈቻቸው ናቸው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












