አዲስ አበባ | ጥር 29፣ 2016| NBC ETHIOPIA -የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለፈው አንድ ዓመት ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች መግለጫ ስጥቷል::

ባለስልጣኑ የሰው ሃይል ማደራጀትን ጨምሮ የህግ ማዕቀፎችን የማዘጋጀት ተግባራትን ማጠናቀቁን ገልፆ ለካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፍቃድ የሚሰጥበትን እና የሚቆጣጠርበትን መመሪያ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።
15 ዓይነት ፍቃዶችን እንዳዘጋጀ የገለፀው ባለስልጣኑ እስካሁን ባለው ሂደት 5 የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ጨምር በርካታ የግል ተቋማት ገበያውን ለመቀላቀል ዝግጁ ናቸው ብሏል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የሼር ሽያጭና ግብይት መመሪያን በጥቂት ቀናት ውስጥ ይፋ ይደረጋል ብሏል::
በፀጋሁን አሰፋ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












