አዲስ አበባ | ጥር 28፣ 2016| NBC ETHIOPIA -“አሁን እንዳለው ስርዓት አልበኝነትና ጥፋት እስር ቢበዛ ኖሮ ፓርክ ሳይሆን እስር ቤት ነበር የምንገነባው። በጣም ብዙ መታሰር የሚገባቸው ሰዎች በየቀኑ ይታለፋሉ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል። “ሆኖም ግን እኛ ፓርክ እንጂ እስር ቤት አልገንባንም”ብለዋል።
ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎች ጉዳይ ላይ ከመርማሪ ቦርዱ ጋር ውይይቶች መደረጉንም በማንሳት፤ “ሪፖርቶች ቀርበውላችዋል” ሲሉ ለምክር ቤቱ አባላት አስረድተዋል።
በእስር ካሉት አብዛኞቹ ወይንም በሺህ የሚቆጠሩት ተምረው ወጥተዋል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ አሁን ላይ በመቶ የሚቆጠሩ ብቻ በእስር ቤት እንደሚገኙ ገልጸዋል።
በእስር ላይ የሚገኙትም “እየተጣሩ፣ እየተማሩ ሊፈቱ ይገባል እንጂ፤ ለደሃ መንግስት እስረኞችን መቀለብ የሚያዋጣ አይደለም” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












