አዲስ አበባ | ጥር 24፤ 2016| NBC ETHIOPIA- በኬንያ መዲና ናይሮቢ የጋዝ ሲሊንደር ፈንድቶ ቢያንስ የሶስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ወደ ሶስት መቶ የሚሆኑ መቁሰላቸው ተገለጸ ።

አደጋው የተከሰተው ጋዝ ጭኖ የነበረ የጭነት መኪና ፍንዳታ ካጋጠመው በኋላ መሆኑን የመንግሥት ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
አደጋውን ተከትሎ በማህበራዊ ገጾች የተለቀቁ ምስሎች አደጋው ባጋጠመበት አካባቢ ያሉ ቤቶች፣ ሕንጻዎች እና ተሸከርካሪዎች በእሳት ሲያያዙ አሳይተዋል።
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው 271 ሰዎች ወደ ተለያዩ ሆስፒታሎች መወሰዳቸውን እና 27 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ እየተፈለጉ መሆኑን የኬኒያ ቀይ መስቀል ማህበር አስታውቋል፡፡
የተቀጣተለው እሳት ወደ ሌሎች የመኖሪያ ህንጻዎች ተዛምቶ ስለነበር የሟቾችን እና የተጎጂዎችን ቁጥር ከፍ ሊያደርገው እንደሚችል ተገምቷል፡፡ ዘገባው የቢቢሲ ነው
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv