አዲስ አበባ | ጥር 16፤ 2016| NBC ETHIOPIA-ንባብ እና ሀገር የተሰኘው 8ተኛው ከተማ አቀፍ የንባብ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ሙዚየም በዛሬው እለት ተከፍቷል።


በመዲናዋ የሚገኙ ወጣቶች እና ተማሪዎች የንባብ ባህላቸውን ለማሳደግ፣ በቤተ-መፅሐፍት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመገንዘብ እና በህትመቱ ዘርፍ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በቅርበት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለመወያየት ፌስቲቫሉ ሰፊ እድልን ይፈጥራል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ የባህል ዘርፍ ምክትል ሀላፊ አስፋው ኩማ ተናግረዋል።
ደራሲያን፣ መፅሐፍ ሻጮች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የግል እና የመንግስት ቤተ መፅሐፍቶችን ጨምሮ ከ50በላይ በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማት በፌስቲቫሉ እየተሳተፉ ይገኛል።

ትውልዱ ጊዜውን ከንባብ ይልቅ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በማሳለፉ መሰል ፌስቲቫሎች መካሄዳቸው አንባቢዎች ለማበረታታት እና ለማነቃቃት እንደሚያችል ተገልጿል።
“አንባቢ ትውልድ ለሀገር ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ፌስቲቫሉ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት በአዲስ አበባ ሙዚየም ለህዝብ ክፍት ሆኖ ይቆያል።
በእለቱ ጥሪ የተደረገላቸው የስራ ሀላፊዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች፣ መምህራን፣ ተማሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ ክፍለ ከተማ የተወጣጡ ታዳሚዎች በፌስቲቫሉ ተገኝተዋል።
በ-ሀሴት ኃይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv