አዲስ አበባ | ጥር 16፤ 2016| NBC ETHIOPIA- በደቡብ ምዕራብ ማሊ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ውስጥ በተከሰተ አደጋ ከ70 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።

በአካባቢው የወርቅ ማዕድን አጥኚዎች ባለስልጣን ኦማር ሲዲቤ በወርቅ ማውጫ ሜዳው ውስጥ ከ200 በላይ የወርቅ ማዕድን አውጭዎች የነበሩ ሲሆን 73 አስከሬን መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
የማሊ መንግስት ለሟች ቤተሰቦች እና ለማሊ ህዝብ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል። በተጨማሪም በማዕድን ማውጫ አቅራቢያ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የደህንነት መስፈርቶችን እንዲያከብሩ እና ለወርቅ መጥበሻ በተዘጋጁ ቦታዎች ላይ ብቻ እንዲሰሩ ጠይቋል። ማሊ ከዓለም ትልቅ ወርቅ ላኪ ሀገር ነች።