አዲስ አበባ | ጥር 15፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ ለመሆን በሚደረገው ትንቅንቅ ዶናልድ ትራምፕ በኒው ሄሚስፌር ድል ቀንቷቸዋል መባሉ ለማሸነፍ ለሚያደርጉት ጉዞ ተስፋ ሰጪ መሆኑ ተገልጿል።

ተፎካካሪያቸው አምባሳደር ኒኪ ሄሊ እጅ አልሰጥም ማለታቸውን ተከትሎ ትራምፕ መሸነፍሽን እመኝ እያሉ ሲወርፏቸው ነበር ተብሏል።
እስካሁን 70 ከመቶ ድምጽ የተቆጠረ ሲሆን ትራምፕ በከፍተኛ ድምጽ ኒኪ ሄሊን መምራታቸው እየተነገረ ነው ። ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












