አዲስ አበባ | ጥር 09፤ 2016| NBC ETHIOPIA -በደቡባዊ ፊሊፒንስ በማዕድን ቦታ በደረሰ መሬት መንሸራተት ሰባት ሰዎች ሲሞቱ ሁለት ቆስለዋል፤ አስር የሚሆኑት ደግሞ መጥፋታቸው ታውቋል፡፡

አደጋው የደረሰው ዳቫዶ ዲ ኦሮ በተባለች ግዛት ከባድ ነፋስ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብና ባስከተለው ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ነው ተብሏል ፡፡
የአካባቢው ባለስልጣናት እንዳስታወቁት በደረሰው አደጋ ከሰው ህይወት በተጨማሪ 1000 ሺህ የሚሆኑ ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል ፡፡
ባለፈው ሳምንት በሰሜናዊ ፊሊፒንስ በደረሰ የመሬት መንሸራተት እና ከባድ ነፋስ ባስከተለው ጉዳት ስምንት ሰዎች ሞተው እንደነበር የዘገበው ሲ ጂ ቲ ኤን ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv











