አዲስ አበባ | ጥር 09፤ 2016| NBC ETHIOPIA – ሰሜን ኮርያ በሁለት ታዳጊዎች ላይ 12 ዓመት ከባድ የጉልበት ስራ እንዲሰሩ ፍርድ ማስተላለፏ ታውቋል፡፡ታዳጊዎቹ ፍርዱ የተላለፈባቸው የደቡብ ኮርያ ፊልም ሲያዩ በመያዛቸው ነው ተብሏል፡፡

የ16 ዓመት ሁለቱ ታዳጊዎች ጥፋታቸውን ያለምንም አቤቱታ እንዲቀበሉ መገደዳቸውም ተግልጿል፡፡
በሰሜን ኮርያ የደቡብ ኮርያ የሆኑ ድራማዎች፤ ዘፈኖችና ሌሎች የመዝናኛ አማራጮች መመልከት ፈጽሞ የተከለከሉ ናቸው፡፡
እንደ ቢቢሲ ዘገባ፤ የደቡብ ኮርያ ተከታታይ ድራማዎች በዓለምአቀፍ ተቀባይነት ያላቸው ቢሆኑም በሰሜን ኮርያ ግን ማየትም ማሳየትም አይፈቀድም ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv











