አዲስ አበባ | ጥር 04፤ 2016| NBC ETHIOPIA – ሳንቲም ፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን አክስዮን ማህበር የመጀመሪያውን የጠቅላላ ጉባኤ አደረገ፡፡
ጉባኤው ላይ ባለፈው አንድ አመት ያከናወናቸውን የተለያዩ ተግባራትን ለባለአክስዮኖች በማቅረብ ውይይት የተደረገ ሲሆን አባላቱ የድርጅቱን ያለፈውን አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ገምግመው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፈዋል፡፡
ደርጅቱ ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ከስድስት ሺህ በላይ ነጋዴዎችን ደንበኛ አድርጎ ከ2 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎችን ያፈራ ሲሆን ከ 6 ቢሊየን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውርን በሳንቲም ፔይ የዲጅታል የክፍያ ሲስተም አማካኝነት መፈፀሙ ተገልጿል፡፡
የሳንቲም ፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን አክስዮን ማህበር ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በሃምሌ ወር 2014 ፍቃድ አግኝቶ ወደ ስራ የገባ ሲሆን ከገንዘብ ንክኪ ነጻ የሆነ ዲጂታል እና የዘመናዊ ግብይት ተጠቃሚ የሆነ ማህረሰብን ለመፍጠርና፤ የክፍያ ሥርዓትን ለማዘመን በተለያዩ ፋይናንሻል መድረኮች እንደ ባንኮች፣ የክፍያ ሞባይል ዋሌት መተግበሪያዎች የክፍያ ስርዓት ላይ እየሰራ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡
ሳንቲም ፔይ በህዳር ወር 2015 ዓ.ም ሦስት ዋና ዋና የቴክሎጂ ምርቶች ፖስ (ተንቀሳቃሽ የክፍያ መተግበሪያ)፣ ዩኒፋይድ ፔይመንት ኢንተርፌስ (ዩ ፒ አይ) (ባንኮችን የሚያስተሳስር የክፍያ ስርዓት) እና ፔይመንት ጌትዌይ (በኢንተርኔት የሚደረጉ ክፍያዎችን የሚያስተሳስር) የተባሉ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶችን ከዘጠኝ አጋር ባንኮች እና ከቴሌብር ጋር በመተባበር ስራ መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












