አዲስ አበባ | ጥር 06፤ 2016| NBC ETHIOPIA – የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ሲደረጉ የአምናዋ ባለክብር ሴኔጋል ከ ጋምቢያ ጨዋታ 11፡00 ይጀምራል።
በአገራቱ ያለፉ 23 የእርስ በእርስ ግንኙነቶች ሴኔጋል አንድም ሽንፈት እንዳልደረሰባት ቁጥራዊ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በአሊዮ ሲሴ የሚመሩት የቴራንጋ አንበሶች በዚህ መድረክ ባደረጓቸው ያለፉ 14 ጨዋታዎች በአልጄሪያ ብቻ ሁለት ጊዜ ተረተዋል።
ዘንድሮ በተከታታይ ለአምስተኛ ጊዜ ነው የዚህ መድረክ ተሳታፊ መሆን የቻሉት።
ጋምቢያ በአንጻሩ በታሪኳ ለሁለተኛ ጊዜ ነው የምትሳተፈው።
ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈችበት ካሜሮን ባዘጋጀችው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር እስከ ሩብ ፍጻሜ መጓዝ ችላ እንደነበር አይዘነጋም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጋምቢያ ብሔራዊ ቡድን አባላት ሐሙስ ዕለት ከመዲናዋ ባንጁል ተነስተው ወደ ኮትዲቯር ሲበሩ የኦክስጅን እጥረት አጋጥሟቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ ወደቆ እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል።
ብሔራዊ ቡድኑን ያሳፈረው አውሮፕላን 9 ደቂቃ አየር ላይ ከቆየ በኋላ ተመልሶ ለማረፍ ተገዷል።
ጊንጦቹ ወዲያውኑ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት አዳማ ባሮው ባዘጋጁላቸው ልዩ አውሮፕላን ያሙሱክሮ መግባት ችለዋል።
አመሻሹን ካሜሮና ከ ጊኒ እንዲሁም አልጀሪያ ከ አንጎላ ይጫወታል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook –https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












