አዲስ አበባ | ታህሳስ 23፤ 2016| NBC ETHIOPIA – ታላቁ ኢትዮ ኢድ- ኤክስፖ “የኢድ ዋዜማዎች በሚሊኒየም” በሚል መሪ ቃል ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 01/2016 በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ተገልጿል::

በባዛሩ ላይ ከ200 በላይ አምራችና ነጋዴዎች ይሳተፉበታል የተባለ ሲሆን ከ300 ሺህ የሚልቁ ጎብኚዎችም ይጎበኙታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተጠቅሷል::
ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 01/2016 በሚካሄደው ታላቁ ኢትዮ ኢድ ኤክስፖ ላይ ቢላል አል ሀበሺ እና ባቡል ኸይር የእርዳታ ተቋም እንደሚሳተፉ ተመላክቷል::

ለልጆች የመጫወቻ እንዲሁም የሰላት መስገጃ ስፍራ እንደሚዘጋጅም ተገልጿል::
በአክረም ኑርያ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












