አዲስ አበባ | ታህሳስ 23፤ 2016| NBC ETHIOPIA – የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ኮኮብ ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ከአሜሪካው ዲ ሲ ዩናይትድ ሃላፊነቱ ከተነሳ በኋላ የሻምፒዮን ሽፑን በርሚንግሃም መረከቡ ይታወሳል።

ይሁንና በሊጉ ካደረጋቸው 15 ጨዋታዎች 10 ነጥቦችን ብቻ ሰብስቦ ክለቡን ለውጤት ቀውስ በመዳረጉ ደጋፊዎችን ጨምሮ በርካቶች ከየአቅጣጫው ሲቃውሙት ሰንብተዋል።
በዚህም የክለቡ የቦርድ ሰብሳቢና ባለድርሻ ቶም ብራዲና ቦርዱ ሩኒን ማሰናበታቸው ተሰምቷል።
የዌስት ሚድላንድሱ ክለብ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጋሪ ኩክ፣ ” በሴንት አንድሪው ስኬት ይሆን ዘንድ አስፈላጊውን ሁሉ ነገር ለማድረግ ቁርጠኛ ነን፣ እንዳለመታደል ሆኖ ከሩኒ ጋር የነበረን ዉል የታለመትን ግብ ስላልመታ በሌላ መንገድ ለመሞከር በመወሰናችን አሰናብተነዋል” ሲሉ በክለቡ ይፋዊ ማህበራዊ የትስስር ገጽ በኩል አስታውቀዋል።
የብቃት አሰልጣኙ ስቲቭ ስፑነር፣ ክለቡን በጊዚያዊነት እንደሚረከቡ በመግልጽ አዲሱን ዋና አሰልጣኝ ከሰሞኑ ይፋ እንደሚያደርጉ አክለዋል።
ከሩኒ መምጣት በፊት 6ኛ ደረጃ ላይ የነበረው በርሚንግሃም ሲቲ በሁለት ወራት ዕድሜ ውስት በአስገራሚ ፍጥነት ቁልቁል ተምዘግዝጎ 20ኛ ላይ ተቀምጧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc












