
አዲስ አበባ | ታህሳስ 17፤ 2016| NBC ETHIOPIA-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የ2ተኛ ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራ ጥሪ መደረጉን አስመልክቶ ቱሪዝም ሚኒስቴር ጥሪ የተደረገላቸዉን እንግዶች ለመቀበል በቀጣዮ ጊዜያት ስለ ታቀዱና ስለሚሆሩ መርሃ ግብሮች ዝርዝር መግለጫዎችን ሰጥቷል።

ይህን አስመልክቶ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ እንዳስታወቁት የዲያስፖራውን የእረፍት ጊዜያቶች አስመልክቶ በቱሪዝም ሚኒስትር የሚመራ በርከት ያሉ ባለድርሻ አካላትም ያሳተፈ አብይ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሰፊ ዝግጅት ሲከናወን መቆየቱን ገልፀዋል::
የጥሪው አላማም በዋናነት የዲያስፖራዉ ወገን ሀገር እና ባህሉን ይበልጥ እንዲያውቅ ለማስቻል ታሳቢ ተደርጎ ነዉ።
በዚህም በውጭ ሀገራት የተወለዱ ሁለተኛው ትውልድ የዲያስፖራ አባላት ከታህሳስ 20 ቀን 2016 እስከ መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም በሶስት ዙር ወደ ሀገራቸው እንዲመጡ ጥሪ ቀርቧል።
በማህሌትግርማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












