አዲስ አበባ | ታህሳስ 17፤ 2016| NBC ETHIOPIA-እየተጠናቀቀ ባለው በፈረንጆች በ2023 በብዛት ከተጫኑ 10 መተግበሪዎች 4ቱ መተግበሪያዎች ሁሉም መሰረታቸው ቻይና ላይ ነው፡፡ በ2023 በብዛት የተጫኑ መተግበሪያዎች 5ቱን ከታች ዘርዝረናቸዋል፡፡
1. ተሙ(Temu)

ተሙ በቻይና ላይ የተመሰረተ የገበያ ቦታ ግዢ መተግበሪያ ሲሆን ምርቶችን በቀጥታ ለተጠቃሚዎች የሚያቀርብ ነው። ግዢ መተግበሪያው ከቤት ዕቃዎች እስከ ጌጣጌጥ እስከ የወጥ ቤት ዕቃዎች ሁሉንም ምርት ያገበያያል ። እንደ አማዞን ካሉ ሌሎች የገበያ ቦታዎች ጋር ሲወዳደር የምርቱ የዋጋው በሚያስደንቅ ሁኔታ ርካሽ ናቸው።
ተሙ በአሜሪካ ውስጥ በመጋቢት 2023 በአፕል አፕ ስቶር እና በጎግል ፕሌይ ስቶር ውስጥ ከ10 ሚሊዮን በላይ መተግበሪያውን አውርደውታል፡፡
2. ቲክቶክ(TikTok)

ቲክቶክ በ2023 በጣም ከወረዱ መተግበሪዎች ሁለተኛ ነው እ.ኤ.አ. በማርች 2023 ቲክቶክ በአሜሪካ ውስጥ ከ7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አውርደውታል፡፡
3. ካፕከት (CapCut)

የቲክ ቶክን ዘላቂ ስኬት ግምት ውስጥ በማስገባት CapCut ፣ የቲክ ቶክ ቪዲዮ ኤዴት ማድረጊያ መተግበሪያ በመሆኑ በ2023 በጣም ከተጫኑ መተግበሪያዎች ዝርዝር ውስጥ ሶስተኛ ሁኗል፡፡
በCapCut ቪዲዮዎችን በቀላሉ ማሳጠር፣ ሙዚቃዎችን እና የትርጉም ጽሁፎችን ማከል እና ቪዲዮዎችዎን በቀጥታ ከመተግበሪያው ማጋራት ይችላሉ። እ.ኤ.አ. ከማርች 2023 ጀምሮ CapCut ከ6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አውርደው ተጠቅመዋል፡፡
4. ሺኢን (SHEIN)

SHEIN አልባሳትን፣ ጌጣጌጦችን እና የቤት እቃዎችን በዝቅተኛ ዋጋ የሚሸጥ የዲጂታል የግዥ መድረክ ነው። በማርች 2023 ይህ መተግበሪያ በአሜሪካ ከ6 ሚሊዮን አውርደው ተጠቅመውበታል፡፡
5. ዋትስአፕ (WhatsApp)

ዋትስአፕ በዓለም ዙሪያ ግንባር ቀደም የመልእክት መላላኪያ መተግበሪያ በማርች 2023 ወደ 6 ሚሊዮን በሚጠጉ ሰዎች መተግበሪያውን አውርደው ተጠቅመዋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












