አዲስ አበባ | ታህሳስ 15፤ 2016| NBC ETHIOPIA – አንዲት ወላድ እናት ከወለደች ከ 4 እስከ 6 ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ የሚከሰት የድብርት ዓይነት ነው ፤ ጊዜውን ገፍቶም አንዳንዴ እስከ 12ተኛው ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ ሊጀምር ይችላል።

ይህ ህመም ከ10-15% የወለዱ እናቶች ላይ ይታያል፡፡ስለሆነም የድህረ ወሊድ ደብርት እንዲከሰት ከፍተኛ አስተዋፅዎ የሚያደርጉ ነገሮች
-በእርግዝና ጊዜ ጨምረው የነበሩ ሆርሞኖች (Estrogen and Progestron) በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ
– ልጅ ከተወለደ በኋላ ተያይዞ የሚመጣ እንቅልፍ ማጣት ትንንሽ ጉዳዮችን በራሳችን ማከናወን እንዲከብደን ስለሚያደርግ ይህም ተስፋ የመቁረጥ እና ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ እየሆኑ እንደሆነ መምሰል፤
-ከእርግዝና በፊት ወይም በእርግዝና ጊዜ የነበረ ጭንቀት ወይም ድብርት
– በበፊት እርግዝና እና ድህረ ወሊድ ላይ ድብርት ከነበረ
-ከዚህ በፊት የነበረ የስነ አእምሮ ችግር ካለ
-ከዚህ በፊት ወይም በእርግዝና ላይ የጤና መታወክ ከነበረ ወይም ደግሞ ከስራ መባረር እና ስራ ማጣት ካለ
-የወለድሽው ልጅ የተለያዩ የጤና እክሎች ካሉት እና የተለየ እንክብካቤ የሚያስፈልገው ከሆነ
-ከአንድ በላይ ህፃን ወልዳ ከሆነ ይህም ለማጥባት እና ለመንከባከብ የሚከብድ ከሆነ
-በመጀመሪያ አካባቢ ጡት ማጥባት የሚያስቸግርሽ ከሆነ
-ከትዳር አጋር ጋር አለመስማማት ወይም መጋጨት ካለ
-አነስተኛ የኑሮ ሁኔታ
-እርግዝናው ሳይታቀድ ፣ ሳይፈለግ እና ድጋፍ ሳይደረግለት ከተከሰተ
የድህረ ወሊድ ድብርትን እንዴት እንከላከለው?

-በግልፅ የትዳር አጋራችንን እና የቤተሰባችንን እርዳታ እንደምንፈልግ መጠየቅ
-ከወሊድ በኋላ ስላሉ ነገሮች ማንበብ ወይም ሀኪምን ማማከር
-በጠዋት ተነስቶ ትንሽም ቢሆን እንቅስቃሴ ማድረግ
-የተመጣጠነ እና የማያጨናንቅ ምግብ መመገብ
– ልክ እንዳንቺ የወለዱ እናቶች ጋር በመደወል ወይም በአካል በመገናኘት ሀሳብ መለዋወጥ እና አእምሮን ዘና የሚያደርጉ ነገሮችን ማድረግ ከድህረ ወሊድ ድብርት ሊገላግለን ይችላል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












