Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አራተኛው ዙር የሶስትዮሽ ድርድር ዙሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ

December 20, 2023
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አዲስ አበባ | ታህሳስ 10፤ 2016| NBC ETHIOPIA- በመግለጫው ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን አራተኛውን ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ላለፉት 3 ቀናት በአዲስ አበባ ማካሄዳቸውን ገልጾ፤ እነዚህ አራት ዙር ድርድሮች የተካሄዱት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና በግብጹ ፕሬዚዳንት ዓብዱል ፋታህ ኤል ሲሲ የጋራ መግባባት መሆኑን አስታውሷል።

ሁለቱ መሪዎች የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ አሞላል እና ዓመታዊ ስራን አስመልክቶ የወጣውን ደንብና መመሪያ አጠናቅቆ ለማስቀጠል አስፈላጊው ሁሉ ጥረት እንዲደረግም ጥረዋል። ይህ ለአራት ዙር የዘለቀው ድርድር ሶስቱ ሀገራት በመካከላቸው ያሉ ዋና ዋና ልዩነት ፈጣሪ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት እንዲያደርጉ ማገዙም እንደማይዘነጋ መግለጫው ጠቁሟል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው በእነዚህ አራት ዙሮች ኢትዮጵያ ከሁለቱ የታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ጋር ዋና ዋና ልዩነቶችን ለመፍታት እና የሰላም ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረት አድርጋለች። በአንፃሩ ግብፅ የቅኝ ግዛት ዘመን አስተሳሰቧን ይዛ በመቀጠል ወደ ስምምነት እና ትብብር የሚደረገውን ጉዞ ተቃውማ መንገድ ዘግታለች ብሏል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ አሞላል እና ዓመታዊ አሰራር መመሪያ እና ደንቦች ላይ የተደረገው ድርድር በሶስቱ ሀገራት መካከል መተማመን ለመፍጠር እንጂ በአባይ ውሃ አጠቃቀም ላይ የኢትዮጵያን መብት ለመንጠቅ ያለመ አይደለም፤ ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቷን በፍትሃዊ እና ምክንያታዊ አጠቃቀም መርህ ላይ በመመሥረት የአሁንና የመጪውን ትውልድ ፍላጎት ለማሟላት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል በግልፅ ማሳወቅ ትፈልጋለችም ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር።

እ.ኤ.አ 2015 ሶስቱ ሀገራት የተፈራረሙት የመርህ ስምምነት ለዚህ ድርድር መሰረት ነው ያለው መግለጫው ከዚህም በላይ ከ2020 ጀምሮ ጉዳዩን የያዘው የአፍሪካ ኅብረት ሦስቱ አገሮች በሰላማዊ መንገድ ወደ መፍትሔ ሀሳብ እንዲመጡ ዕድል የሚፈጥርበትን መድረክ ማመቻቸቱን አስታውሷል።

ላለፉት 3 ቀናት የተካሄደው አራተኛው ዙር ድርድር ከተጠናቀቀ በኋላ ግብፅ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ቻርተር እና የአፍሪካ ህብረት ህገ-መንግስታዊ ድንጋጌን የሚጻረር መግለጫ አውጥታለች ያለው መግለጫው ኢትዮጵያ በግብፅ በኩል የቀረበባትን የተሳሳተ መረጃም አትቀበልውም ብሏል።

ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ እና በፍትሐዊ ድርድር የሶስቱን ሀገራት ጥቅም የሚያስጠብቅ የመፍትሔ ሀሳብ ላይ ለመድረስ ያላትን ቁርጠኝነት ይዛ እንደምትቀጥልም የውጭጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል።

YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA

TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia

Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/

Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv

#NBC_ETHIOPIA

#ሆኖ_መገኘት

ShareTweetShare
Previous Post

የኢትዮ-ሩስያ የጋራ ኮሚሽንና ቢዝነስ ፎረም

Next Post

ከ6.3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የገበያ ማዕከላት ተገንብተው መጠናቀቃቸውን አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ከ6.3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የገበያ ማዕከላት ተገንብተው መጠናቀቃቸውን አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ

ከ6.3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የገበያ ማዕከላት ተገንብተው መጠናቀቃቸውን አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ

የኮሎራዶ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትራምፕን ከገዛቲቱ የምርጫ ውድድር ሰረዘ

የኮሎራዶ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትራምፕን ከገዛቲቱ የምርጫ ውድድር ሰረዘ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት 26ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት 26ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?