አዲስ አበባ | ታህሳስ 09፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያዘጋጀው የኢትዮ-ሩስያ የጋራ ኮሚሽንና ቢዝነስ ፎረም እየተካሄደ ነው፡፡


የኢትዮ-ሩስያ የጋራ ኮሚሽንና ቢዝነስ ፎረም ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚ ፣ሳይንቲፊክ፣ በቴክኒካል እና በንግድ ትብብር እንዲሁም በባህል እና ቱሪዝም ዙሪያ ምክክር በማድረግ ስምምነት ይፈራረማሉ ተብሏል።
ፎረሙ ሁለቱ አገራት ያላቸውን ግንኙነት ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሳደግ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርና የኢትዮ-ሩስያ የጋራ ኮሚሽን ሰብሳቢ ዶክተር በለጠ ሞላ ተናግረዋል።
አገራቱ እምቅ ሃብት ቢኖራቸውም በተለይም በንግድና ኢንቨስትመንት ዙሪያ ባላቸው አቅም ልክ እየሰሩ ባለመሆኑ ትብብሩን ለማሳደግ ከዚህ የበለጠ መስራት አለባቸውም ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ በግብርና፣ በአምራችና በማዕድን ዘርፎች ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ መኖሩን ጠቁመው የሩስያ ባለሃብቶች እነዚህን እድሎች ተጠቅመው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሰብለ ወንድማገኝ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook –
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












